በመንግሥት እና በፋኖ መካከል የሚካሄደዉ ጦርነት የአማራ ክልል ንግድን ማቀዛቀዙ
ሰኞ፣ መጋቢት 29 2017በመንግሥት እና በፋኖ መካከል የሚካሄደዉ ጦርነት የአማራ ክልል ንግድን ማቀዛቀዙ
በአማራ ክልል በመንግስትና በፋኖ ሀይሎች መካከል እየተካሄደ በሚገኘዉ ጦርነት ምክንያት የንግድ ስራዉ መቀዛቀዙ ተገለፀ። ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ የመንገድ መዘጋት ዝርፊያና የማህበረሰቡ የመሸመት አቅም ዉስንነት ነጋዴዎችን ከንግድ ስራ እያስወጣ መሆኑም ተነግሯል። የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች በበኩላቸዉ አሁን በአማራ ክልል ያለዉ የንግድ መቀዛቀዝ በአጠቃላይ የሀገር ኢኮኖሚ ላይ ተፅኖ ይኖረዋል ብለዋል።
በአማራ ክልል በመንግስትና በፋኖ ሀይሎች መካከል እየተካሄደ በሚገኘዉ ጦርነት ምክንያት የንግድ ስራዉ መቀዛቀዙ ተነገረ። ሁለት ዓመት ሊሞላዉ የተቃረበዉ በአማራ ክልል በመንግስትና በፋኖ ታጣቂ ሀይሎች መካከል እየተካሄደ የሚገኘዉ ጦርነት በክልሉ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ የሆነ ተፅኖ እንደፈጠረ በአምራች በአከፋፋይና በችርቻሮ ንግድ የተሰማሩ ነጋዴዎች ይናገራሉ።
«የሆነ ሰዉ ሲያልፍ ከኔ ገባ ከኔ ገባ እያልን ነዉ አሁን የምንሰራዉ ገብቶሀል በቀን አንድ ሰዉ ሁለት ሰዉ ከገባ በጣም ነዉ የምናመሰግነዉ ከዚያ ዉጭ እጂ ሳንፈታ የምንገባበት ጊዜ ነዉ አሁን><በቀን ሁለት መኪና ሦስት መኪና ልንሸጥ እንችላለን አሁን ግን ከጦርነቱ በኃላ ምንም አይነት እንቅስቃሴ የለም የሚታሰበዉ ወጭ እንጂ ገቢ እንኳን ያን ያክል ነዉ የሚገዛም የለም»
በክልሉ ያለዉ ግጭት በንግዱ ዘርፍ ላይ ያሳደረዉ ተፅኖ በንግዱ ማህበረሰብላይ ከፍተኛ ኪሳራ እንዲኖር አድርጓል የሚሉት አስተያየት ሰጭዎች በበኩላቸዉ፤ የነዳጅ ዘይት እጥረትና የዋጋ ንረት በአማራ ክልል
«እኛ በወር ዉስጥ ሦስት አራት መኪና እያስመጣን ከኛ እየተረከብ የሚያከፋፍሉ ነበሩ ለነሱ ሁሉ እናከፋፍል ነበር በደምብ እንሸጥ ነበር አሁን ላይ ያለዉ ሁኔታ ግን በሁለትም በሦስትም ወር አንድ መኪና መጨረስ አልቻንም አሁን የተረፈን የቤት ኪራይ የሰራተኛ እና ሌሎች ወጭዎች ናቸዉ >< እኛ አሁን አዕምሯችንን ያሳመነዉ በቃ ጦርነት አለ ብለን እራሳችንን ስላሳመነዉ ነዉ ጥሩ ነዉ የምልህ እንጂ በጣም የሞተ ሽያጭ ነዉ እየሸጥን ያለነዉ»
አሁን በአማራ ክልል ካለዉ ግጭት ጋር ተያይዞ ምርት በሚፈለገዉ መጠንና ቦታ እየደረሰ አይደለም የሚሉት አስተያየታቸውን ለዶቼቬለ የሰጡ የንግድ ፈጣሪዎች በየቦታዉ ያለዉ ተደጋጋሚ ቀረፅ የዋጋ ንረት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል ይላሉ፤ «የጦርነቱ ሁኔታ ሰላሙም ስሌለለ መንገድ የመዘጋቱ የመዘረፉም ሁኔታ ስላለ ነጋዴዉ እንደፈለገ ማለፍ አይችልም ቀረፅ አለ መንገድ ላይ የሚከፈል ግብር አለ የኪስ አለ ያን ያንን አልፎ ነዉ ነጋዴዉ በጣም ወጭ አብዝቶ ስለሚሄድ ያንን አስቦ ለህዝቡ ያደርሳል»በአማራ ክልል የአፈር ማዳበሪያ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ አለዉ ሲሉ አርሶደሮች ቅሬታ አቀረቡ
የነጋዴዎች ከንግድ ስራዉ ማቋ ረጥ
ተደጋጋሚ ጦርነት በሚያስተናግዱ አካባቢዎች ያሉ ነጋዴዎች የህብረተሰቡ የመሸመት አቅም ከመዳከሙ ጋር ተያይዞ የንግድ ስራ እስከማቆም እንደደረሱም ተነግሯል። «አሁን አንዳንድ ስዎች እኛ አካባቢ ስራ እየተዉ እየለቀቁ ነዉ የቤት ኪራይ ብቻ መክፈል እናም ግብሩም የቤት ኪራዮም ሲሆን በርካታ ሰዉ ከስራዉ ዉጭ ሆኗል»
በአማራ ክልል የተፈጠረዉ የንግድ መቀዛቀዝ እንደ ሀገር ተፅኖዉ የጎላ መሆኑ
በአማራ ክልል ባለፉት 20 ወራት በመንግስትነና በፋኖ ታጣቂ ሀይሎች መካከል እየተካሄደ በሚገኘዉ ጦርነት በክልሉ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ የፈጠረዉ ክፍተት ከክልሉ አልፎ እንደ ሀገርም ከፍተኛ ጫና አለዉ የሚሉት በመቅደላ አምባ ዮንቨርስቲ የምጣኔ ሀብት መምህር የሆኑት አቶ ብሩክ ወንዴ ናቸዉ።
«ጫናዉ በጣም ከፍተኛ ነዉ ምን አልባት በአማራ ክልል ብቻ አይደለም በሀገሪቱ ላይ ነዉ በጣም ከባድ የሆነ ጫና ነዉ ያለዉ በሁሉም ዘርፍ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በአገልግሎት በግብርና ዘርፍ እንደፈለገ ማዘዋወር አይችልም ሰዉ ያመረተዉን»
በክልሉ አሁን የተፈጠረዉ የዋጋ ንረት ከተጠበቀዉ በላይ መሆን የአማራ ክልልን ጥቅል የኢኮኖሚ ሁኔታ ተገማች እንዲሆን አላደረገዉም የሚሉት የምጣኔ ሀብት መምህሩ በፖሊሲ ካልታገዘ በስተቀር የዋጋ ግሽበቱን ማሻሻል ከባድ ነዉ ብለዋል።«መፍትሄ ለመዉሰድ በጣም የረፈደ ይመስለኛል የዋጋ ግሽበት በጣም አደገኛ ነዉ የዋጋ ግሽበት የሚባለዉ በፐርሰንት ነዉ 10ፐርሰንት 20 ፐርሰንት አሁን እኮ 500,300,ፐርሰንት እየተባለ ነዉ የሚገለፀዉ እንዲህ የሚባል መለኪያ የለም ይሄ ያረጋገዋል ለማለት ምናልባት መለኪያ የለዉም በጣም ከባድ ነዉ በፖሊሲ ነዉ ሊፈታ የሚችለዉ»በአማራ ክልል የዋጋ ንረትና ጫናው
በአማራ ክልል ያለዉ የንግድ ሁናቴ ጤነኛ ያለመሆን በአጠቃላይ የሀገር ዉስጥ ምርት ላይ የሚፈጥረዉ ተፅኖ መሆኑ ኢኮኖሚዉን በቀጥታ እንደሚጎዳዉ አቶብሩክ ወንዴ ይናገራሉ፤
«በሀገር ዉስጥ ምርት ላይ የሚፈጥረዉ የሚፈጥረዉ ተፅኖ በጣም ከፍተኛ ነዉ ስለዚህ እንደ ሀገር በብዙ መንገድ ከግብርና በአምራችና በአገልግሎት ዘርፉ ድምር ነዉ ስለዚህ የአማራ ክልል ሲቀነስ አስበዉምን ሊፈጥር ይችላል እንዃን አይደለም እዚህ ሰፊ ቦታ ላይ የሆነች ጠባብ ቦታ ላይ እረብሻ ካለ እንዃን ተፅኖዉ የሚታወቅ ነዉ»
ኢሳያስ ገላዉ
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ