በለንደን የዩክሬን ደጋፊ አገራት መሪዎች ጉባኤ
ሰኞ፣ የካቲት 24 2017በለንደን የዩክሬን ደጋፊ አገሮች መሪዎች ጉባኤ
በለንደን የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስተር ኬይር ስታርመር አስተናጋጅነት የተካሄደው ዋናዎቹ የዩክሬን ደጋፊ አገሮች መሪዎች ጉባኤ ዩክሬንን በወታደራዊና ፋይናናስ የበለጠ ለመርዳት ተስማምቶ የተነሳ መሆኑ ተገልጿል።ይህ ከአውሮፓ ህብረት ውጭ የካናዳንና የኖርዌይ መሪዎችን እንዲሁም የቱርክን የውጭ ጉዳይ ሚኒስተርን ያካተተው የበርክታ የአውሮፓ አገሮች መሪዎች ጉባኤ፤ ባለፈው አርብ በኋይት ሀውስ በፕሬዝዳንት ዝለንስኪና ፕሬዝዳንት ትራምፕ መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ ተከትሎ የተክሄደ ነው።
ጉባኤው የደረሰበት ስምምነት
በስብሰባውም መሪዎቹ የአውሮፓ አገሮች የመክላከያ አቅማቸውን ለማስደግና ለዩክሬን የሚሰጡትን እርዳታም ለማሳደግና የሰላም ዋስትና ለመስጠት የተስማሙ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስተር ስታርመር ከስብሰባው በኋላ በሰጡት ጋዤጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል። “ የዩክሬንን ስላም ለማስጠበቅና የሚደረገውን የሰላም ስምምነት ዋስትና ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑ አገሮችን ቁጥር እያደገ ነው። ብርታኒያ በበኩሏ ወታደቿን በምድርም በአየርም ለማሰማራት ፈቃደኛ ነች” በማለት ለዩክሬንም ሆነ አህጉራችን ሰላም ዋስትና ግን የአሜሪካ ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸውል።
የኋይት ሀውሱ ውዝግብ ሊያስክትል የሚችለው የዲፕሎማሲ መዘዝየትራምፕ እና ዜሌኒስኪ ውዝግብ
ሦስት ዓመት የዘለቀውን የሩሲያና ዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለመምከር ባለፈው ዓርብ ዋሽንግተን የተገኙት ፕሬዝዳንት ዘለነስኪ በኋይት ሀውስ ከፕሬዝዳንት ትራምፕና ባለስልጣኖቻቸው ጋር የነበራቸው ቆይታ ዓለምን ባስገረመና ባስደገጠም ሁኔታ ባለመግባባት መቋረጡ ፤በዩክሬን ስላም ብቻ ሳይሆን በአውሮፓና አሜርካ ወዳጅነትና ግንኑነት ላይም ትልቅ ጥያቄ የሚያስነሳ ሁኗል። ውዝግቡን ተክትሎ በርካታ የአውሮፓ መሪዎች ለፕሬዝዳንት ዘለነስኪ ድጋፋቸውን የገለጹ ቢሆንም፤ አለመግባባቱን በማስወገድ የአሜሪካንን ድጋፍና ትብብር ማረጋገጥ ግን አስፈላጊና ወሳኝም እንደሆነ በጉባኤው እንደታመነበት ነው የተገለጸው። በዚህ በኩል በተለይ ጠቅላይ ሚንስተር ስታርመርና ፕሬዝድንት ማክሮን ልዩ ጥረት እንደሚያደርጉና ከዩክሬን ጋርም አማራጭ የሰላምና የሰላም አስከባሪ ሀይል ዕቅድን ለአሜሪካ እንዲያቀርቡ የታሰበ መሆኑም ተገልጿል።
የጉባኤው ውጤት
ሆኖም ግን የትኞቹ አገሮች ወታደሮችን ለማሰማራት ፈቃደኛ እንደሆኑንና ያለ አሜሪካ ድጋፍም በተለይ ያየር ክልሉን የማስጠበቁ ስምሪት የመቻል አለምቻሉ ሁኒታ በዝርዝር እንዳልታይ ነው የተነገረው።የትራምፕ ርምጃና የአዉሮጶች ዛቻ
በአጠቃላይ ግን የስብሰባው ተሳታፊዎች ከሁሉም በፊት የአገሮቻቸውን የመካላከያ ወጪ በማሳደግ የራሳቸውን ደህንነት ለማስጠበቅ ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው አምነውበታል ተብሏል። የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝድንት ወይዘሮ ኡርሱላ ቮንዴር ለየር ከስብሰባው በኋላ በሰጡት መግለጫም አውሮፓ እራሱን እንደገና ማስታጠቅ ያለበት መሆኑን አስታውቀዋል።
የስሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ ዋና ጸሀፊ ማርክ ሩተም ከስብሰብው በኋላ በስጡት አስተያየት ጉባኤው አስፈላጊና የተሳካ እንድነበር ተናግረዋል፤ “ በጣም ጥሩ ስብሰብ ነው። ምክኒያቱም ብዙዎች አገሮች ለዩክሬን የሚስጡትን እርዳታ አጠናክረው ለማስቀጠልና የሰላም ስምምነት ከተደረገም ለዩክሬን የሰላም ዋስትና ለመስጠት ፈቀደኛ መሆናችው የታየበት ነው” ብለዋል።
ተጠባቂ ውጤት
በአሜሪካ በኩል ዩክሬን የቀረበውን የሰላም ሀሳብና ስምምነት የምትቀበል ክሆነ ድጋፏን ልትቀጥል እንደምትችል መገለጹ የሚነገር ሲሆን ፕሬዝድንት ዘለነስኪም የአሜሪካንን ድጋፍና ትብብር አጥብቀው እንደሚሹ ነው የሚታወቀው።፡ በሌላ በኩል በለንድኑ ጉባኤ ከስምምነት የተደርሰባቸው የሰላም ሀስቦችና እቅዶች ብዙም ግልጽ እንዳልሆኑ ነው የሚነገረው። በመጨው ሀሙስ የሚካሄደው የ27ቱ አባል አገሮች መሪዎች ጉባኤ ግን በዚህ በኩል በጥልቀት በመያየት ወሳኝ እርምጃዎችን ይወስዳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ የብርታኒያው ጠቅላይ ሚስተር ሚስተር ስታርመርና ፕሬዝዳንት ማክሮንም በፕሬዝዳናት ትራምፕና ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት በማስወገድ በዩክሬን ጉዳይ በአውሮፓና አሜሪካ መካከል የተፈጠረውን ልዩነት ሊያጠቡ ይችላሉ ተብሎም ተስፋ ተደርጓል።
ገበያው ንጉሴ
አዜብ ታደሰ
ታምራት ዲንሳ