በባቲ ከተማ የተጣሉት የሰዓት እላፊ ገደቦች
ዓርብ፣ ነሐሴ 30 2017በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የባቲ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት ባደረገዉ አስቸኳይ ስብሰባ የተለያዩ ክልከላዎች ጣለ። ምክር ቤቱ በአካባቢዉ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችን ለመቆጣጠር የወጣ ክልከላ ነዉ ብሎል። በአካባቢዉ የኦነግ ሸኔ እንቅስቃሴ አለ ተብሏል። በከተማው የሰዉን እንቅስቃሴን በተመለከተ ማንኛዉም ሰዉ ከምሽቱ 4:00 ሰዓት በኋባ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርግ ተከልክሏል። በተጨማሪም የባጃጂ ትራንስፖርት ከ12 ሰአት በኃላ መንቀሳቀስ ታግዶል። ምክር ቤቱ ውሳኔዎቹን ተላልፎ የተገኘ ማንኛዉም አካል በህግ ጥላ ስር በመቆየት ተጠያቂ ይደረጋል ሲል አስጠንቅቋል።
በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር የባቲ ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት በከተማዋ የሚደረጉ የታጣቂዎች እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር የሰዓት እንቅስቃሴ ገደብ ጥሏል፡፡ በከተማዋ አቅራቢያ ባሉ የገጠር ቀበሌዎች የታጣቂዎችእንቅስቃሴ አለ የሚሉት የከተማዋ ነዋሪዎች በተደጋጋሚግለሰቦች ለጥቃት ሲጋለጡ ተስተውሏል ብለዋል፡፡ አስተያየታቸውን ለዶቼቬለ የሰጡ እና ስማቸው እንዳይገለፅየፈለጉ የከተማ ነዋሪ ታጣቂዎች የብልጽግና ፓርቲ ደጋፊ የሆኑነዋሪዎችን ትኩረት ያደረገ ጥቃት ይፈጽማሉ ይላሉ፡፡
‹‹ባቲ በስተ-ሰሜን እና በስተ-ምስራቅ ባሉ ገጠራማ አባቢዎች ላይ የሸኔ ታጣቂዎች ይንቀሳቀሳሉ በተለያየጊዜምግጭቶች ማህበረሰቡ ላይ ይደርሳሉ፤ በተለይማህበረሰቡ የብልጽግና ፓርቲ ደጋፊ ሆኖ ከተገኘ ሰዓትበመጠበቅበእላፊ ሰዓት በመምጣት ግለሰቦችንየማጥቃት፣ ንብረቶችን የመዝረፍ ነገር እየሰማን ነው፡፡›› በባቲ ወረዳ ታጣቂዎች 3 ሰዎችን ገደሉ
በባቲ ከተማ የሰዓት እላፊ ክልከላ ያስከተለዉ ተፅኖ
በባቲ ከተማ የሰዓት እላፊ እንቅስቃሴ ገደብ ባለፉት 2 ዓመታት በተደጋጋሚ ይጣላል ያሉት ሌላው የከተማው ነዋሪም የትራንስፖርት የሰው እንቅስቃሴ መገደቡ ከፍተኛ ጫናፈጥሮብናል ብለዋል፡፡ ‹‹በጣም ቆየ 2 ዓመት አለፈው ገደብ ከተጣለ ትራንስፖርት የለም፤ ብዙ ተፅዕኖ ነው እየደረሰብን ያለው፤ ከ12፡00 ሰዓትበኋላ የባጃጅ ተሸከርካሪ አይንቀሳቀስም አሁን ደግሞከ3፡00 በኋላ እግረኛ መንቀሳቀስ አይችልም፤ የታመመሰው፤ ነፍሰ ጡርም በጣም ፈታኝ ነው ያለው ሁኔታ፡፡››
የግለሰቦች ለጥቃት መዳረግ
በባቲ ከተማ እና ዙሪያው የሚስተዋሉ የህዝብን ሰላምየሚያደፈርሱ ተግባራት ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል የሚሉትአስተያየት ሰጭም እርስ በእርስ የሚያጋጩን ፍላጎቶችንየማስታረቅ ተግባር መሰራት አለበት ሲሉ ይገልፃሉ፡፡ ‹‹እርስ በእርሳችን እንድንጣላ፣ እንድንተላለቅ የሚያደርጉንሰዎች ከድርጊታቸው መቆጠብ አለባቸው፤ ጥያቄካለጥያቄያቸውን ሰላማዊ በሆነ መንገድ መጠየቅ፣ አለብን፡፡››
የሰዓት እላፊ ገደብም ጥሰዋል የተባሉ የማህበረሰብ ክፍሎችበፀጥታ ሀይሎች ድብደባ ይፈፀምባቸዋል የሚሉት የከተማውነዋሪ በሰዓት እላፊ ገደቡ ምክንያት ከ12፡00 በኋላ መንቀሳቀስአስቸጋሪ ነው ይላሉ፡፡ ‹‹ከእርምጃም በላይ የመደብደብ እርምጃ ይወሰዳል ምንምምክንያት ለህዝቡ አልተገለፀም እንደፈለጉ ናቸው፤ማንኛውም እንቅስቃሴ ከ12፡00 በኋላ አስቸጋሪ ነው፡፡›› በባቲ ከተማ የተጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ የከፋ ነገር ተፈጥሮየተጣለ ሳይሆን አንዳንድ አመላካች ጉዳዮች ለሥጋት ስለዳረጉንነው የሚሉት የባቲ ከተማ ከንቲባ አቶ አብዱ አህመድበአካባቢው የሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ቡድን የተደራጀ እና አቅምያለው አይደለም ይላሉ።በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ልዩ ዞን በቦምብ ጥቃት 5 ሰዎች መቁሰላቸውን የአማራ ክልል አስታወቀ
‹‹ሰዓት እላፊ እንቅስቃሴውም ከሰሞኑ ስለሰጋን የተጣለነው፡፡ ምንም የተፈጠረ ነገር የለም፤ ከ4ሰዓት በኋላየሰውእንቅስቃሴ እንዳይኖር ነው፡፡ የከፋ ነገር የለም፤ ኦነግ ሸኔምየተደራጀ እና አቅም ያለው አይደለም፤ በሚኒሻኦፕሬሽንእየተሰራበት ነው፡፡›› በባቲ ወረዳ ገጠራማ ቀበሌዎች ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂቡድኖች በተበታተነ ሁኔታ እንጂ የተደራጁ ባለመሆናቸውማህበረሰቡን ለሥጋት የሚዳርግ ምንም ችግር የለም የሚሉትአቶ አብዱ አህመድ የተጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ ለጥቂት ጊዜብቻ የሚቆይ ነው ብለዋል፡፡ ‹‹በቁጥጥር ስር ያደረገው ቀበሌ የለውም፤ ተደራጅቶ ሀይልሲመጣበት የሚገጥምም አይደለም፤ አምስት ሁለትእየሆኑመንገድ ላይ ይሹለከለካሉ፤ እየተደበቁ ይህንን ያህልየሚያስፈራ አይደለም፤ አሁን ወቅቱ ክረምትበመሆኑአረንጓዴ መልበስ ስላለ ለዚያ ብለን ነው ምንም የሚያሰጋነገር የለም፤ የሚቆይም አይደለም፡፡››
ኢሳያስ ገላዉ
አዜብ ታደሰ
እሸቴ በቀለ