ምያንማር ውስጥ በችግር ላይ የነበሩ 32 ኢትዮጵያውያን አዲስ አበባ ተመለሱ
ሰኞ፣ መጋቢት 1 2017ከእገታ ወጥቶ ለሀገሩ የበቃው ወጣት ምን አለ?
ለጎብኝዎች የሚሰጥ የይለፍ ማረጋገጫ - ቪዛ ተዘጋጅቶለት፣ የአውሮፕላን ቲኬት ቆርጦ ወደ ታይላንድ የተጓዘው ወጣት ከዚያም ሜሶት ወደሚባል ቦታ የስምንት ሠዓት ጉዞ ሲያደርግ የሚጠብቀው የተሻለ ገቢ የሚያስገኝ ሥራ እንጅ ስቃይ እንደሆነ አልጠበቀም ነበር። ይህ ዛሬ አዲስ አበባ ከገቡት 32 ወጣቶች መካከል የሆነው ሰው ገንዘብ ለቤተሰቦቹ ሠርቶ መላክ ባለመቻሉ የፈጠረበት ጭንቀት ስሙን ለዚህ ዘገባ እንዳንጠቅስ አድርጎታል። ይህ ወጣት ምያንማር በነበረበት ወቅት ከተፈፀመበት ግፍ ባልተናነሰ ለቤተሰቦቹ ሰርቶ ገንዘብ አለመላኩ ሌላ ይህም ሆኖበታል። ወጣቱ ለመሥራት ያሰበውን ሥራ ባይከውን እንኳን የጤናውን ኹኔታ አደጋ ላይ ለሚጥል ፈተና የተሞላበት ሕይወት ይጋለጥ እንደሆን ቀድሞ አልገመተም ነበር።ምያንማር ውስጥ ለችግር የተጋለጡት ኢትዮጵያውያን
"ፈጽሞ ተገላቢጦሽ፣ ከእውነት የራቀ ውሸት ውስጥ ነው የደረስነው።"
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር "ሕንድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በምያንማር በእገታ ሥር ቆይተው ወደ ታይላንድ ከተሻገሩ 133 ኢትዮጵያ መካከል 32ቱ ዛሬ ወደ አገራቸው የገቡ ሲሆን 43 ኢትዮጵያውያንን ደግሞ ዛሬ ምሽት ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።" ሲል ዛሬ ማለዳ አስታውቋል።
ለተሻለ ሥራ በሚል ወደዚያች የሩቅ ምሥራቅ ሀገር የተጓዘው ወጣት እንደሚለው የብዙ የተማሩ ሰዎች ጭንቅላት ለጉዳት ተዳርጓል። "የብዙ ወጣቶች አዕምሮ፣ የብዙ ምኁራን ጭንቅላት ብዙ የተደረገበት - በኤሌክትሪክ ንዝረት አንስቶ" ስቃይ ደርሶብናል ብሏል። ምያንማር ውስጥ ለፈተና የተዳረጉት ኢትዮጵያውያን ጉዳይ
ወደፊት ይመጣሉ የተባሉት ኢትዮጵያውያን
ቤተሰቦቻቸው ወደ ምያንማር የሄዱ ሰዎች መንግሥት በሚቻለው ጥረት ሁሉ ከስቃይ እንዲያስወጣቸው ብርቱ ውትወታ ሲያደርጉ ቆይተዋል። ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተደጋጋሚ በመሄድም አቤት ብለዋል። ከእነዚህ መካከል አንዷ ብዙ ብሥራት ትገኝበታለች። ወንድሟ ከነገ ወዲያ ረቡዕ እንደሚመለስ ማረጋገጧን በደስታ ስሜት ውስጥ ሆና ነግራናለች። "መቼ እንደሚመጡ፣ ስንት ሰዓት እንደሚመጡ የሚያሳየውን መረጃ ከአየር መንገድ አግኝተናል።" ብላለች። ምያንማር የተቃርኖ ሕብር ሐገር
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥረቱን እንደሚቀጥል አስታውቋል ። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር "ቀሪዎቹ በታይላንድ ማቆያ የሚገኙ 58 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ" ጥረት እየተደረገ ነው ብሏል። ብዙ ብሥራት እንደምትለእ ግን አሁንም እዚያው ምያንማር ውስጥ ያሉት ወጣቶች በተቻለ ፍጥነት ሊወጡ ይገባል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር "ሕብረተሰቡ በሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ሀሰተኛ ቅስቀሳ ተታሎ የሥራ ስምሪት ውል ወደ አልተፈፀመባቸው ሀገራት ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እንዲቆጠብ" አሳስቧል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ