ምርጫ ጀርመን 2025 ዉጤት
ሰኞ፣ የካቲት 17 2017ማስታወቂያ
የምርጫ ጀርመን 2025 የድምጽ ቆጠራ መጠናቀቁን ተከትሎ የፍሬድሪክ ሜርስ የወግ አጥባቂው የክርስትያን ዴሞክራት ፓርቲ እና የእህት ፓርቲ የክርስትያን ዴሞክራት ህብረት አሸንፈዋል። ተጣማሪዎቹ ወግ አጥባቂ ፓርቲዎቹ አሁን የሚቀራቸው መንግስት ለመመስረት የተጣማሪ ፓርቲ ንግግር ነው።
በውጤቱ መሰረት የክርስትያን ዴሞክራት ፓርቲ እና የእህት ፓርቲ የክርስትያን ዴሞክራት ህብረት 28.6% በማግኘት ሲያሸንፉ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ ድምጽ ያገኘው አማራጭ ለጀርመን ፓርቲ ኤ ኤፍ ዲ 20.8 % በመቶ በማግኘት ሁለተኛ ሆኗል። የመራሔ መንግስት ኦላፍ ሾልስ ፓርቲ ሶሻል ዴሞክራት በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ዝቅተኛ ድምጽ ያገኘበትን ደግሞ 16.4 % በማግኘት ሶስተኛ ሆኗል። በዉጤቱ መሰረት ምክር ቤቱን ወንበሮች የተቀራመቱ አምስቱ ፓርቲዎች ተለይተዋል።
አሁን ጥያቄው አሸናፊው የወግ አጥባቂ ፓርቲ ህብረት ከየትኞቹ ፓርቲዎች ጋር ተጣምሮ መንግስት ይመሰርታል የሚለው ሆኗል።