ምርጫ ጀርመን 2025 ምን አዲስ ነገር አስከተለ?
ሰኞ፣ የካቲት 17 2017ምርጫ ጀርመን 2025 ምን አዲስ ነገር አስከተለ?
የብርቱዋ እመቤት አንጌላ ሜርክል ፓርቲ የክርስትያን ዴሞክራት ህብረቱ ፍሬድሪክ ሜርስ የመራሔ መንግስትነታቸው ጉዳይ የተረጋገጠ እየሆነ ነው። በጀርመን የግራ ዘመም ፖለቲካ አራማጆችን ያሳላፋችሁት ሶስት ዓመታት ዉጤት አላመጣም በዚህም «መቀጠል አትችሉም» በማለት ብርቱ ትችት ሲሰነዝሩ የነበሩት ሰው አሁን ጀርመንን የመምራት ዕድል ወደ ማግኘት እየተሸጋገሩ ነው። ወግ አጥባቂዎቹ ከሶሻል ዴሞክራት ፓርቲ ጋር የጥምር መንግስት መመስረት የሚሳችላቸውን ንግግር ይጀምራሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው። ለዚህም ሜርስ «ዓለም ቆማ አትጠብቀንም፤ ጊዜ የለንም » እያሉ ነው።
ምናልባትም በተጣማሪዎቹ መካከል ንግግሩ በአስቸኳይ ከተጀመረ እስከፊታችን የፈረንጆቹ የፋሲካ በዓል መንግስት የመመስረቱ ሂደት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። ከ20 በመቶ በላይ ድምጽ ማግኘት የቻለው የቀኝ ዘመሙ ኤ ኤፍ ዲ በጥምር መንግስት ውስጥ እንደማይካተት አስቀድሞ ታውቋል። የወጣት ጀርመናዉያንን ድምጽ በከፍተኛ ደረጃ ማግኘት የቻለው ግራ ዘመሙ ፓርቲም በድጋሚ በምክር ቤቱ ውስጥ ተከስቷል። በአንድ ወቅት ጀርመንን ይመራ የነበረው በክርስትያን ሊንዴ የሚመራው የኤፍ ዲ ፒ ፓርቲ አምስት ከመቶ የመራጮችን ድምጽ ማሳካት ባለመቻሉ ሊንዴ ከስልጣናቸው እንዲለቁ ጭምር ምክንያት ሆኗቸዋል።
ታምራት ዲንሳ
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር