27ተኛው የተመ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ
ማክሰኞ፣ ኅዳር 6 2015ማስታወቂያ
ሀያ ሰባተኛው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ተከታታይ ዓመታዊ ጉባኤ ዛሬ ሻርምኤልሼክ ግብጽ ውስጥ ተጀምሯል። በዘንድሮው ጉባኤ ቁጥራቸው ወደ አንድ መቶ የሚጠጋ የሀገራትና የመንግሥትት መሪዎች ተሳትፏል ።ጉባኤው ከባቢ አየርን የሚበክሉ ጋዞች መጠን ቅነሳንና በዓለም ሙቀት መጨመር ምክንያት ችግር ውስጥ የወደቁ ታዳጊ ሀገራትን በገንዘብ የመደገፍ ጥያቄን የመሳሰሉ ጥሪዎች ይተላለፉበታል ተብሎ ይጠበቃል። የዓለማችን ሀብታም ሀገራት ከዛሬ 13 ዓመት አንስቶ በአየር ንብረት ለውጥምክንያት የተከሰቱና ወደፊትም ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ለመቋቋም የሚውል የ100 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ለደሀ ሀገራት ለመለገስ ቃል ቢገቡም እስካሁን ተግባራዊ አልሆነም። ዛሬ ስለተጀመረው ስለዚሁ ጉባኤ የዶቼቬለ አማርኛው ክፍል የጤናና አካባቢ ፕሮግራም ዋና አዘጋጅ ሸዋዬ ለገሠ ጉባኤዉ ዋና ርዕስ ስላደረገዉ ጉዳይ ከባልደረባዋ ኂሩት መለሰ ጋር አጠር ያለ ቃለ ምልልስ አድርጋለች።
ሸዋዮ ለገሠ
ኂሩት መለሠ