20ኛው በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን የባህል እና ስፖርት ዝግጅት
ዓርብ፣ ነሐሴ 2 2017ማስታወቂያ
20ኛው በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን የባህል እና ስፖርት ዝግጅት በጀርመኗ የንግድ ከተማ ፍራንክፈርት በቅርቡ ተካሂዷል። በዚህ ዝግጅት ለመሳተፍ ከተለያዩ የአውሮጳ ሃገራትና የአስተናጋጇ ሀገር የጀርመን ከተሞች የመጡ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ፍራንክፈርት ከተማ ላይ ታድመዋል።
በዓመታዊው ድግስ ለታዳሚዎች ከሚዘጋጁ የባህል እና የስፖርት ውድድሮች በተጨማሪ ባህላዊው ምግብና መጠጥ በየፈርጁየሚታይበትና የሚቀመስበት ልዩ አጋጣሚ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ።በሀገርኛ ጭፈራ እና ሙዚቃም የማይረሳ ጊዜ ማሳለፋቸውን ገልፀዋል።የዘህ ሳምንት የባህል መድረክ ዝግጅት በጥቂቱ ቃኝቶታል።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ፀሀይ ጫኔ