ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የገቢ እና የወጭ ንግድ የጭነት አገልግሎት የሚከናወነው በዚህ የጅቡቲው የቀይ ባሕር የውኃ አካል ላይ ነው። የሀገሪቱ ወደቦች ይህንን ባሕር ተንተርሰው የሚገኙ ናቸው።ሞቻ ደሴት በጅቡቲ ሥር የሚገኝ እና ከጅቡቲ ከተማ የባህር ዳርቻ በሦስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ የሀገሪቱ የደሴት አካል ነው።
ይህ በታጆራ ባሕረ ሰላጤ መሀል ላይ የሚገኘው ደሴት ብዙ ነዋሪ የሚኖርበት ባይሆንም አሁን አሁን ግን የመዝናኛ አማራጭ የመሆን እድሉ እየሰፋ ይገኛል።
ቀይ ባሕር ቀላል መጠን የሌለው የዓለም ንግድ መሳለጫ መስመር ሲሆን፣ የንግድ መርከቦች የደረቅ እና እንደ ነዳጅ ያሉ መሰረታዊ የፈሳሽ ሸቀጦች መዘዋወሪያም ስፍራ ነው።
ቪዲዮ: ሰለሞን ሙጩ