የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢው ምን አሉ?
ዓርብ፣ ግንቦት 29 2017ማስታወቂያ
አቶ ሰለሞን አየለ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ናቸው ። ለዴቼ ቬለ የአንድ ለአንድ ዝግጅት በሰጡት ቃለ ምልልስ ምክር ቤቱ ከስልሳ በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ የመሰረቱት ምክር ቤት እያከናወነ ያለውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ነግረውናል።
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎች አጀንዳዎችን ለሔራዊ የምክክር ኮሚሽን አስረከበ
ወቅታዊ ሀገራዊ የጸጥታ እና የደህንነት ሁኔታ ከሰላማዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰላማዊ ትግል አንጻር እንዴት እንደሚታይ ፤ በቀጣዩ ዓመት ሊካሄድ ቀጠሮ ስለተያዘለት የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ምርጫ እና አስቻይ ሁኔታዎች በስፋት ተዳሰዋል።
ስድስት የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ አዳዲስ ሥራ አስፈፃሚዎችን የተመረጡበትን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትን ጉባኤን ውጤት አንቀበልም አሉ
የፖለቲካ ፓርቲ አመራር እና አባላት እስር እና የቢሮ መዘጋት በምርጫው ላይ ሊያሳድር ስለሚችለው ተጽዕኖ እና የምክር ቤቱ ሚናም ተቃኝቷል።
በቅርቡ በምርጫ ቦርድ የተሰረዘው የህወሓት ጉዳይም ተነስቷል። ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ተግባራት እና የምክር ቤቱ ሚና እንዲሁም የገዢው ፓርቲ ከምክር ቤቱ ጋር ያለው ግኙነት እና አንድምታው የተመለከቱ ጉዳዮችም በቃለምልልሱ ከተዳሰሱ ጉዳዮች ተጠቃሹ ነው ።
ታምራት ዲንሳ
ሸዋዬ ለገሰ