የጀርመን የምርጫ ዝግጅት እና የትውልደ አፍሪቃ ፖለቲከኞች ተሳትፎ
ቅዳሜ፣ የካቲት 8 2017ማስታወቂያ
ጀርመን አጠቃላይ ምርጫ ለማድረግ ከአስር ቀናት ያነሰ ጊዜ ቀርቷታል። ለምርጫው የሚደረገው ዝግጅትም በዚያው ልክ ተጧጡፎ ቀጥሏል። ፓርቲዎች የምረጡኝ ዘመቻቸው አጠናክረዋል። የምርጫው ቀን እየቀረበ በሄደ ቁጥር የቀኝ አክራሪ ጽንፈኞችን የሚቃወሙ ድምጾችም ተበራክተው እየተሰሙ ነው።
በጀርመን ፖለቲካ ውስጥ የነቃ ተሳትፎ የሚያደርጉት ትውልደ አፍሪቃ ጀርመናዉያንም እንደ ሌሎቹ ሁሉ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል። የዶቼ ቬለ የአፍሪቃ ቋንቋዎች የጋዜጠኞች ቡድን በጀርመን የተለያዩ ግዛቶች ተዘዋዉሮ እየተደረገ ያለውን የምርጫውን ዝግጅት ተመልክቷል። ፖለቲከኞች እና መራጮችን አነጋግሯል። የአማርኛው አገልግሎት ክፍል ባልደረባ ዮሐንስ ገብረእግዚአብሄር ከቡድኑ ጋር ተጉዞ ሲመለስ ስቱዲዮ ተገኝቶ በአጭሩ ሃሳቡን አካፍሎናል።
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
ታምራት ዲንሳ