የጀርመን እና ሴራሊዮን ሁለትዮሽ ግንኙነት ወዴት?
ቅዳሜ፣ ግንቦት 1 2012ማስታወቂያ
የጀርመን እና ሴራሊዮን የሁለትዮሽ የልማት ግንኙነት ሊቋረጥ መሆኑንን ጀርመን አስታውቃለች። ሴራሊዮንን ጨምሮ በ24 ሃገራት የሁትዮሽ ግንኙነቱን ለማቋረጥ መወሰኗን ያስታወቀችው ጀርመን የድንገተኛ እና አስቸኳይ ድጋፍን ግን እንደማይመለከት አስታውቃለች። ከሌሎች ሃገራት ጋር የሚኖረው ቀጣይ ግንኙነትም በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ እንደሚሆን ገልጻለች።